Get Mystery Box with random crypto!

ኒሂሊዝም (Nihilism) የተባለው ፍልስፍና መሰረቱ፣ ጥቅሙስ ምንድን ነው? --- ኒሂሊዝም የሚባ | ጥበብ

ኒሂሊዝም (Nihilism) የተባለው ፍልስፍና መሰረቱ፣ ጥቅሙስ ምንድን ነው?
---
ኒሂሊዝም የሚባለው ፍልስፍና በአውሮፓ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳ ርዕዮትነው። ኒሂሊዝም እንደሚገለፅበት አውድ እና ዲሲፕሊን የተለያዩ መልኮች ቢኖሩትም ማጠንጠኛው “ክህደት” ሲሆን ሃይማኖት፣ ዕምነት፣ ባህል፣ እውቀት፣ ሕግ፣ ሥነ ምግባር ወዘተ በጠቅላላው በኒሂሊዝም ይካዳሉ። ኒሂሊዝም መሠረቱ ጥርጥር (skepticism) ነው። ጥርጥር ዓላማው ውሸትን ለይቶ እውነት ጋር መድረስ ነው። ጥርጥር ግን በወለደችው ኒሂሊዝም የተሰኘ ልጅ ዓላማዋንም ትርጉሟንም አጥታ እየሞተች ነው። ጥርጣሬ ጫፍ ሲይዝ እና ጨለምተኛነት የሚባል ቅመም ተጨምሮበት ሲበስል ኒሂሊዝምን ይወልዳል። ኒሂሊዝም ሁሉንም ነገር ያለምህረት መካድ ነው። በኔ በኩል ጥቅም አለው ብዬ አላስብም። የአብዘርድ አቀንቃኙ ካሙ እንኩዋን፣ እውነት ነው ህይወት ትርጉም የላትም፣ ግን ትርጉም የላትም ብለን ልንተዋት አይገባም፣ ትርጉም ልንፈጥርላት ግድ ነው ይለናል።

የሰው ልጅ በማህበራዊ ኑሮ ዉስጥ ህልውናውን የሚያስጠብቅባቸው፣ ባህሉን የሚያስከብርባቸውና ለትውልድ የሚያስተላልፍባቸው፣ ዕውቀቱን የሚያሰፍርባቸው፣ ስሜቱን የሚገልጽባቸውና ሥነ-ምግባሩን የሚተረጉምባቸው እሴቶች አሉት፡፡ እነዚህ እሴቶች የሰው ልጅ የፈጠራቸው እና ለእነዚህ ዕሴቶች ተገዥ ሆኖ የሚኖርባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል አንድ ማህበረሰብ እንደ ማኅበር ራሱን የሚገልጥበትና ህላዌውን የሚያዘልቅበት ባህል አለው፡፡ ባህል ለተፈጥሮአዊ ጉዳዮች የሚሰጥ “ምላሽ” (expression) ነው፡፡ እምነት፣ ሃይማኖት፣ እውቀት፣ ሞራል፣ ልማድ፣ ህግ/መተዳደሪያ ደንብ፣ ኪነ-ጥበብ፣ ምርትና ማምረቻ መሳሪያ፣ አልባሳት፣ ወዘተ. . . የባህል ዘርፎች ናቸው፡፡ በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ባህል አለ። ማህበረሰብ ለባሕል ያለው አመለካከት የተለያዬ ቢሆንም ለዕሴቶቹ እውቅናን መስጠት ብቻ ሳይሆን አስፈላጊነታቸውንም ያምናል፡፡ ነገር ግን ኒሂሊዝም እነዚህን ሰዋዊ እሴቶች ይክዳል፤ አላስፈላጊነታቸውንም ይሰብካል፡፡ መሰረት የሌላቸውና አንዳችም ጥቅም የማይሰጡ መሆናቸውን በመግለጽ በሰው ልጅ ህላዌ ውስጥ ያላቸውን ህልውና ይክዳል።

ኒሂሊዝም ሕይወት ትርጉም የለሽ እንደሆነ በማመን፣ ሁሉንም ሃይማኖታዊ እና ሥነ ምግባራዊ መርሆች አለመቀበል ነው፣ ልቅ የሆነ ነፃነት ይኑርም፣ ሁሉንም ከዜሮ እንጀምረው ይላል። የሰውን ተፈጥሯዊ ምንነት ካለማወቅ የሚመነጭ የጥፋት መንገድም ይመስላል። ሰው በcognitive evolution ያገኘውና ከሌሎች እንሰሳት የለየው ነገር ቢኖር የሌለን ነገር በ association በአዕምሮው መፍጠር መቻሉ ነው። ነገር ግን ኒሂሊስቶች በዚህ መንገድ የተፈጠረው ይጥፋና በሌላ ተጨባጭ እውነት ይተካ ይላሉ። በመጀመሪያ ይህን የማይጨበጥ እውነት እንዴት ለማጥፋት ይቻለናል? ከተቻለስ፣ ሰው እራሱ መልሱ እንደማይፈጥረው ምን እርግጠኛ አደረገን?

አንግዲህ ይህ ሃሳብ ነው የኢትዮጵያ ችግር መፈቻ ቁልፍ ሆኖ በአለማያው ገላገይ፣ በዚህ መጽሐፍ ዘንድ የቀረበው። መጽሐፉ ሙሉውን አጥፍተን ከዜሮ እንጀምር አይነት አቀራረብ ያለው፣ አለምን በጠባብ መነጸር ያየ ነው። ስራን (ባርነትን) የድህነት መውጫ መንገዶ አድርጎ ገልጾ ግን ያለውን መንፈሳዊ እውቀት ይጥፋ ይለናል፣ የሚተካውን የእውቀት መንገድ ግን አላሳየንም። የችግሩን መንስኤዎች በሙሉው የሚያሳይም አይደለም። እናም መፍትሔ ጠቋሚ አይደለም። ጥሩ ጥያቄ፣ የመፍትሔው መንገድ ግን የጎደለና በሾርኔ አይቶ ወይም ሳያይ ያለፈ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ችግርን በቃላት ድርድራ አንፈታውም። ትክክለኛውን የሃሳብ መንገድ አላገኘውም እያልኩ ነው። ችግራችን የምንፈታው፣ በዚህ አይነት የመንስኤ-ውጤት ግንኙነትን በሚያጣርስ፣ ሁሉ ይጥፋ ከዜሮ እንጀምር በሚል ሃሳብ አይደለም። የችግራችን መንስኤዎች ብዙ መሆናቸውን መለየት፣ መፍትሔም ከዚህ አንፃር መፈለግን ይጠይቃል። እናም ስንጽፍ ብቻ ሳይሆን አስተያየት ስንረጥም ይህን ያገናዘበ መሆን አለበት። ከመጽሐፉም፣ ከውይይቱም ግን ይህን አላየሁም። ከዜሮ መጀመር መፍትሄ አይደለም። መፍትሄው ያለንን ጥሩ፣ ከመጥፎው መለየት። የጎደለውን ከአለም ዘንድ መፈለግና ለእኛ ችግር መፍቻ በሚሆን መንገድ መቅረጽ፣ ሁለቱን ለንቅጦና የእኛ አድርጎ መጠቀም ነው። ይጥፋ አብዮት ወይም ኒሂልስም ነው፣ ጥፋት። ከጥፋትም ልማት አይገኝም።

አለማየሁ ገላጋይ
የተጠላው እንዳልተጠላ