Get Mystery Box with random crypto!

የሕይወት ስንቅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fikreayele — የሕይወት ስንቅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fikreayele — የሕይወት ስንቅ
የሰርጥ አድራሻ: @fikreayele
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 394
የሰርጥ መግለጫ

ለሕይወት ስንቅ የሚሆነውን ዕውቀት መጨበጥ

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-20 07:52:16 በዜሮ የተባዛው አገልግሎት!

አንድ ንጉስ አስር አመት ሙሉ በታማኝነት ያገለገለው አገልጋዩ እንዲት ስህተት ስለሰራ ብቻ ቅጣትን አስተላለፈበት፡፡ በንጉሱ ሕግ መሰረት ማንኛውም ስህተት የሰራ አገልጋይ በኃይለኛነታቸውና በተናካሽነታቸው የታወቁት የንጉሱ ውሾች ወደሚኖሩበት ግቢ ለቅጣት ታልፎ ይሰጣል፡፡

ይህንን የንጉሱን ውሳኔ የሰማው ታማኝ አገልጋይ በሁኔታው በጣም አዘነ፡፡ እሱን ያሳዘነው የተላለፈው ቅጣት ሳይሆን፣ ለአስር አመታት ካለምንም ስህተት አገልግሎ፣ አንዲት ስህተት ብቻ ስለተገኘችበት የንጉሱ መጨከን ነው፡፡

ይህ አገልጋይ ቁጭ ብሎ፣ “ይህንን ቅጣት አስቀረሁትም፣ አላስቀረሁት ንጉሱ ግን ይህንን ጥሩ ያልሆነ ልምምድ የሚያቆምበትን አንዲት ትምህርት ባስተምረው ደስ ይለኛል” ብሎ አሰበና አንድ ብልሃት መጣለት፡፡

ንጉሱንም፣ “ቅጣቱን እቀበላለሁ፣ ቅጣቱ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ግን አስር ቀን ይሰጠኝና ከዚያ በኋላ በፈቃዴ ለቅጣቱ እመጣለሁ” ብሎ ጠየቀው፡፡ ንጉሱም ፈቀደለት፡፡

በእነዚህ አስር ቀናት ለውሾቹ የሚሆንን ምግብ አዘጋጅቶ እነሱ ያሉበት ግቢ በመሄድና ቀስ ብሎ በመቅረብ እያበላቸው፣ እየተንከባከባቸውና እያሻሻቸው በሚገባ ካገለገላቸው በኋላ በአስረኛው ቀን ወደ ንጉሱ መጣ፡፡ ፍርዱ አልቀረለትም ነበረና ወደውሾቹ ግቢ እንዲጣል ትዝዛዝ ተላለፈበትና ተጣለ፡፡ ውሾቹ ለአስር ቀን የተንከባከባቸውንና ያገለገላቸውን ይህንን ሰው ምንም ነገር አላደረጉትም ነበር፡፡

ንጉሱም ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ሁኔታ በመሆኑ ተገርሞ አስጠራውና የተፈጠረውን ጠየቀው፡፡ አገልጋዮም፣ “ንጉስ ሆይ፣ እርሶን አስር አመት በታማኝነት አገልግዬ አንዲት ጥፋት ስለተገኘብኝ ብቻ ያ ሁሉ ታማኝነቴና አገልግሎቴ ተረሳና ምህረትም አላገኘሁም፡፡ እነዚህ ውሾች ግን ለአስር ቀናት ብቻ ስላገለገልኳቸው ምንም እንኳን ጥፋተኛ ሆኜ ለእነሱ ታልፌ ብሰጥም ያንን አገልግሎቴን ባለመርሳት ምንም አላደረጉኝም” አለው ይባላል፡፡

ንጉሱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህንን ባህሪውን ለማረም ክፍት ወደመሆን እንደመጣ ይነገራል፡፡

ሰዎች ያሳዩንን የብዙ ዓመታት ታማኝነትና አገልግሎት በአንዲት ስህተት ምክንያት በዜሮ አናባዛው፡፡ ይቅርታን እንልመድ! ለሰዎች ሁለተኛ እድልን መስጠትን እንልመድ! ውለታ ቢሶች አንሁን!

@fikreayele
@fikreayele
@fikreayele join us
101 viewsFikre Ayele, 04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 06:24:49 "ከውሻ እና ከ አቦሸማኔ የቱ ሊፈጥን ይችላል?" ተብሎ በዓለም ላይ ካሉ ፈጣን የውሻ ዝርያወች ተመርጠው ከአንድ አቦሸማኔ ጋር የውድድር ፕሮግራም ይደረጋል።

ውድድሩ ሲጀመር ውሾቹ ተፈትልከው ሲሮጡ አቦሸማኔው ስንዝር ያህል እንኳአ ለመሮጥ ፍላጎት አላሳየም።
በዚህ የተገረሙት ታዳሚዎች የውድድሩን አላፊ "አቦሸማኔው ለምን ሊሮጥ አልሞከረም?" አሉት።

አላፊውም "አንዳንዴ ምርጥነትህን_የማይገባ (የማይመጥንህ) ቦታ ላይ ለማሳየት መሞከር የስድብ ያህል ነው" አላቸው።
Don't prove your self every where' ማንነትህን በማንኛውም ቦታ ላይ ለማሳየት አትሞክር።
ምክንያቱም እንደ አቦሸማኔ የሆነ አቅምህን ከውሾች ጋር አውርደህ አትፎካከር።

ወዳጄ ሁሉም ነገር ቦታ እና ጊዜ አለው
በልክ እና የእውነት እንኑር

@fikreayele @fikreayele
@fikreayele @fikreayele
1.4K viewsFikre Ayele, 03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 20:21:45 Don't think the people around you are constantly watching you, noticing all your faults and memorising all your words...

People are fixated on their own problems. They spend most of their time thinking about themselves, even when they pretend to listen to you.

So relax and take it easy. There is no reason to be afraid of communication or public speaking. People pay much less attention to you than you think they do.

@fikreayele
@fikreayele
1.2K viewsFikre Ayele, 17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 07:56:40 ለሌለህ ስትለፋ ያለህን አትርሳው፡፡ምስጋና የስኬት ነዳጅ ነው፡፡የደስታም ምንጭ ነው፡፡በማመስገን የምትከስረው ነገር የለም፡፡
"ይህንና ያን ስጠኝ !!" ብሎ ከማለቃቀስ "ይህንና ያን ስለሰጠኽኝ ተመስገን" ማለት የተሻለ ነው::
-
አግኝቶ ማመስገን ሳይሆን አመስግኖ ማግኘትን ልመድ::
-
መጥፎ ነገር ቢሆንብህ እንኳን "ተመስገን!! ለበጎ ነው!" በል::ምስጋናህ የችግርህን እሳት የሚያጠፋ ውሃ እንደሆነ ተረዳ:: ወደ ፈጣሪህ የሚያቀርብ ማግኔት እንደሆነም እወቅ::
-
ማማረር እና ማለቃቀሱ ይብቃ::ውስጥህን ከማጥቆር ሌላ ምንም ጥቅም የለውም::
-
ከ24ቱ ሰዓት ደቂቃዎችን ውሰድና የህይወትህ በጎ ገፅታዎች ላይ እያተኮርክ በስሜት አመስግን:: ልብህ በደስታ ይሰክራል::በእያንዳንዱ ሰከንድ እያመሰገንከው ብትኖር ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስበው::

መልካም እሁድ

@fikreayele
@fikreayele
@fikreayele join us
1.3K viewsFikre Ayele, 04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 06:24:51 እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚደክም ሳይሆን የሚፈካ በረከት ያግኛችሁ። ከአንደበታችሁ የጥበብ ቃል አይታጣ። እግዚአብሔር የእምነትና የውሳኔ ሰው ያድርጋችሁ። ሀዘን በእናንተ ይገፈፍ። የደከመ ይበርታባችሁ። ሐይላችሁ ዕለት ዕለት ይታደስ። አምላኬ በበዛ ትህትና በበዛ ፍቅር በበዛ ገርነት ይባርካችሁ። እግራችሁ እንደ ዋላ እግሮች ግንባራችሁ እንደ ቡላ ድንጋይ ፊታችሁ እንደ ወጋገን ያድርገው። ነገራችሁን ከቀን ወደ ቀን ይጨምር። ሳትናገሩ በሚናገር ህይወት እግዚአብሔር ይባርካችሁ። እግዚአብሔር የአንደበታችሁን ቃል ያፅና። የእጆቻችሁን ስራ ይባርክ ። የልፋታችሁን ውጤት በዕጥፍ ይስጣችሁ። መልካም ጊዜ

@fikreayele
@fikreayele join us
1.7K viewsFikre Ayele, 03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 18:23:06 የዋህነት ማለት ክፋትን በክፉ ለመመለስ ሙሉ ሀይል ይዞ ነገር ግን ሀይል ለክፋት ላለመጠቀምና እራስን መግዛት ማለት ነዉ።የዋህ ማለት ሞኝ ማለት ሳይሆን ሀይል እንዳለዉ እያወቀ ሀይሉን ለክፋት ሳይሆን ለመልካምነት ብቻ ለመጠቀም የወሰነ እራሱን የሚገዛ ማለት ነዉ፡፡

በየዋህነት ዉስጥ ደሞ ጥሩነት ወይም መልካምነት አለ።መልካምነት እንደወጥ ማጣፈጫ ጨዉ ማለት ናት ማንም ሰዉ በዉስጡ መልካምነት ሳይኖረዉ ደስተኛ መሆን፡መርካት፡ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፡ጤናማ መሆን አይችልም።ምክንያቱም መልካምነት ሀገር የለዉም ድንበር የለዉም ጥቁር ነጭ አይልም በነፃ አገልግሎት ወገንን ማስደሰት ሁል ጊዜ ለሰዉ በመስጠት በማድረግ እንጂ ዉለታ የማይጠብቅ እራስ ወዳድነት የማይሰማዉ ልዩ ነዉ መልካምነት።የሚገርመዉ መልካምነት ሁሌ በመስጠት በማድረግ የሚረካ ሲሆን ትርፉም የህሊና ሰላም ደስታ ፍቅር ጤና ብቻ ብዙ ነገር እናገኝበታለን ።

ታድያ ይሄ ደስ አይልም?
መልካም ነገር ማድረግ ባንችል እንኳን ከመጥፎ ስራዎች እንቆጠብ

ሰናይ ጊዜ

@fikreayele
@fikreayele
1.7K viewsFikre Ayele, 15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 13:52:48 ​ #ሂወት_ይቀጥላል
አንዳንዴ ሂወት ውስጥ እንዲህ ያጋጥማል
እንዳሰብከው ሳይሆን አንተ እንደጠበከው
ፍፁም ተቃራኒ ሁኖ ነው ሚገኛው
ጎንህ ላለው በርቶ ላንተ ይጨልማል
ሌትተቀን እየጣርክ ትርፍህ ድካም ሁኗል
ያቀድከው ያለምከው አልሳካ ብሎህ
መጣ ያልከው ቀርቶ፣ ደግ ያልከው ከፍቶብህ
የኔ ያልከው ወዳጅ ፣ የሩቅ ሰው ሁኖብህ
ውስጥህ ብቸኝነት ፣ ተሞልቶ ባዶነት
ድንግርግር ብሎህ ትርጉሙ የሂወት
በቃ ሁሉም ነገር ስልችት ብሎሀል
ከተስፋ መቁረጥ ስር ካፍፉ ቁመሀል …
,
,
ልብ በል ወዳጀ ሂወት_ይቀጥላል
ጨለማን ባናቅ ኑሮ እኮ የብርሀንን ዋጋ ባልተገነዘብን ነበር ፣ ማጣትን ባናይ ኑሮም
የማግኛት ትርጉም በቅጡ ባልገባን ነበር ፣ የደግ_ሰዎችን ግምት አንድታቅ
የሚያደርጉህም #የክፉወች መኖር ነውኮ።
ሁሉም የሚሆንበት የራሱ ምክንያት አለው
አየህ የሂዎት ገፆች ብዙና የተለያዩ ናቸው ሁሉም ገፆች መልካምና_ጥሩ እንዲሆኑ ግን
መጠበቅ የለብህም። የንጋቱዋን ፀሀይ ለመሞቅ የለሊቱን ጨለማ በትግስት ማሳለፍ ግድ
ነው ።
ልብ_በል ባንተ መቆም የሚቆም ባንተ መኖር የሚኖር ቢያንስ አንድ ሰው አለ ስለዚህ
የፈለገውን ያክል ነገሮች አሰልቺ ቢሆኑብህ እንኳ ተስፋ_መቁረጥን የመጨረሻ ምርጫህ
እንኳ አታድርገው ። ከፈጣሪህ አትራቅ ፣ ዛሬ ላይ ማድረግ ያለብህን ካንተ የሚጠበቀውን
እያደረክ ነገን መልካም እንደሚሆን ተስፋ አድርግ ።ማን ያቃል ባልጠበከውና ባላሰብከው
መንገድ ሂወት በራሷ የተቃናች ትሆን ይሆናል ምክንያቱም ሂወት_ይቀጥላል ።


የሕይወት ስንቅ
ይቀላቀላሉን
@fikreayele
@fikreayele
@fikreayele
276 viewsFikre Ayele, 10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 09:51:44 ልታደርገው የምትችለውን ማንኛውንም ነገር ወይም እችለዋለሁ ብለህ የምታስበውን ነገር አሁኑኑ ጀምረው ምክንያቱም ድፍረት በዉስጡ ብልሀት,ሀይል እና ምትሃትን ይይዛል።አስብ ዉሀዉ ዉስጥ ዘለህ ካልገባህ መዋኘት እንደምትችል በምንም ተአምር ልታቅ አትችልም።አዉቃለሁ መስመጡ, የዉሃዉ ቅዝቃዜ ሌላም ሌላሌ ነገሩ ሊያስፈራህ ይችላል።አስታዉስ ነገሮች እስከሚቻሉ ድረስ የማይቻሉ ሆነው መታየተታቸዉን ሊቀጥሉ ይችላሉ።የሂወት አላማ እምቅ ችሎታህን አሟጦ መጠቀም ነው ።እጥረት የፈጠረ አእምሮ መትረፍረፍን መፍጠር ግን አያቅተዉም!!!


መልካም ሰንበት !

@fikreayele
@fikreayele
@fikreayele
223 viewsFikre Ayele, 06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 06:42:50 የቤተሰብህን ውለታ ለመክፈል ትልቅ ቤት እስክትገነባ አትጠብቅ፡፡ቤቱን ለማግኘት ስትሮጥ ቤተሰብህን ብታጣ ልብህ ይሰበራል፡፡አሁን ባለህበት ቦታ ቤተሰብን ማስደሰት ትችላለህ፡፡በትልቅ ብሎኬት ከተሰራ ቤት በላይ ከቤተሰብህ ጋር የምታሳልፈው አብሮነት ብዙ ዋጋ አለው፡፡ለቤተሰብህ ትኩረት ስጣቸው፡፡ልክ እንደ ልጅነትህ አድምጣቸው፡፡በእነሱ በኩል ወደዚህ ህይወት ስለመጣህ አመስግናቸው፡፡ልክ ፍቅረኛ ወይም ጓደኛህን ጋ ደውለህ ደህንነታቸውን እንደምትጠይቀው ቤተሰብህንም ጠይቃቸው፡፡ይደሰቱ፡፡እዚህ ምድር ላይ የተለየ ሰው ሆነው ይሰማቸው፡፡ምክንያቱም እኒህ ሰው ቤተሰቦችህ ናቸው፡፡እናንተ ከፍ ብላችሁ እንድትታዩ ዝቅ ብለው በለፉ ቤተሰቦቻችሁ አትፈሩ፡፡እነሱ የምንጊዜም ምርጥ ኩራታችሁ ናቸው፡፡ቤተሰቦቻችሁ ምንም ባያደርጉላችሁም አትዘኑባቸው፡፡ምክንያቱም ከምንም በላይ ውድ የሆነውን ህይወት ያገኛችሁት በእነሱ በኩል ነው፡፡ፍቅር ስጧቸው፡፡ተንከባከቧቸው።

የሕይወት ስንቅ
ይቀላቀሉን @fikreayele @fikreayele @fikreayele
247 viewsFikre Ayele, 03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 06:03:11 #የአንተን_ውድቀት_ለሚመኙ_ስትል_ራስህን_አሻሽል!!"
☞ህይወት በውሳኔ የተሞላች ናት፡፡በተለይም አንዳንድ ጊዜ በህይወትህ ውስጥ እንቅፋት የሚሆኑብህንና ደስታህን የሚያጨልሙብህን ሰዎች ካንተ ዘንድ ማራቅ የግድ ነው፡፡

ይህን ማድረግ ካቀተህ የህይወት ፈተናዎችህ ጉልበት እንዲኖሯቸው አቅም እየሰጠህ መሆኑን እወቅ!"
ራሱን ያወቀ ሰው ሁልጊዜ በኑሮው ደስተኛ ነው!!
ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር ማንነትህን ታጣና ህይወት ጣእሟን ታጣለች!


የሕይወት ስንቅ

@fikreayele
@fikreayele
1.2K viewsFikre Ayele, 03:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ