Get Mystery Box with random crypto!

#ተዘርተው_በሚያፈሩበት_ጊዜ_ስናያቸው • በጥቂት ጊዜ ተዘርተው የሚያፈሩት ግንቦት ተዘርተው በሰኔ | ፍቃዱ ሲሳይ የተለያዩ መጣጥፎች፣ግጥሞች ፣ የአመታዊ ክብረ በዓላት ወረቦች እና ታሪካዊ ቦታዎች በምስል

#ተዘርተው_በሚያፈሩበት_ጊዜ_ስናያቸው
• በጥቂት ጊዜ ተዘርተው የሚያፈሩት ግንቦት ተዘርተው በሰኔ የሚበቅሉ በትንሽ ዝናብ ፍሬ የሚሰጡ ሲሆን ይህ ባጭር ጊዜ መከራ የጌታን መንግስት የሚወርሱ ሰማዕታትን ያመለክታል በላይሰብን እና ፈያታዊ ዘየማንን አብነት እናደርጋለን፡፡
በግንቦት ተዘርተው በሌላኛው ዓመት ሐምሌ የሚያፈሩ ደግሞ የጌታችንን መንግስት ለመውረስ ብዙ ፈተናን መከራን የሚያዩ ቅዱሳን ምሳሌ ናቸው እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ እንደ ኢዮብ ብዙ ደዌ ብዙ ስቃይ ያዩ የቅዱሳን ሰማዕታት ምሳሌ ናቸው፡፡
ምነው ጌታችን ሰውን በክብር አበላለጠው ቢሉ ይኸስ እንደልቡናው ፅናት እንደ አእምሮው ስፋት ነው ጌታ የሚችሉትን መከራ ይስጣል እንጂ የማይችሉትን አይሰጥምና ነው፡
• እነዚህን ሁሉ ያስገኘች ምድር ሰውን ትመሰላለች ሰው በሦስት ነገር ፀንቶ ይኖራል 1) በአጥንት 2) በጅማት 3) በደም እንዲሁም ምድር እንደ አጥንታችን ድንጋይ እንደጅማታችን ስር እንደ ደማችን ውሀ ይመሰላሉ የማክሰኞ ዕለት ፍጥረታት በእመቤታችንም ይመሰላል አምላካችን ደግሞ በዘር የማክሰኞ ፍጥረትን ምድር ምግብ የሚሆኑ አዝርዕት፣ አትክልት፣ ዕፅዋትን እንዳስገኘች እመቤታችንም ለሰው ልጅ ሥጋውን ደሙን ምግበ ነፍሰ አድርጎ የሰጠንን ክርስቶስን “እንበለ ዘር” (ያለ ወንድ ዘር) አስገኝታለች “ዘር ያልዘሩበት እርሻ አንቺ ነሽ የሕይወት ፍሬ ካንቺ ወጣ /ውዳሴ ማ ዘማክሰኞ/
• ምድር የእመቤታችን ምሳሌናት በሶስት ነገሮች እንደፀናች ሁሉ በድንጋይ፣ በስር፣ በውሃ እመቤታችንም በሦስቱ በአብ- በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ለመፅናቷ ምሳሌ ነው፡፡
አብ በየማኑ ከደነኪ
ወልድ አደረብሽ
መንፈስ ቅዱስ ፀለለብሽ አነፃሽ (አንቀጽ ብርሃን


ይኽ ከክፍል 4 የቀጠለ ነው ክፍል 5 የረቡዕ ሥነ ፍጠረት ነው ይቀጥላል......