Get Mystery Box with random crypto!

እየጦሙ አለመጦም (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) ተወዳጆች ሆይ እየጦሙ | ትምህርተ አበው

እየጦሙ አለመጦም


(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

ተወዳጆች ሆይ እየጦሙ የጦምን ፍሬ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።ይህስ እንደምን ነው? ያላችሁኝ እንደሆነ:-

ከምግብ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኋጥያት ያልተከለከልን እንደሆነ።

ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደሆነ።

ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፋ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደሆነ።

ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውሃ ርቀን በአይናችን ክፉ ከማየት ያልጦምን እንደሆነ።

ስለዚህ እየጦሙ እንዲህ አለመጦም እንዳለ ተረዱ።


ዲ/ን ፍቃዱ ጎንፋ (ዘፍቁረእግዚእ)
ግንቦት 8/2014