Get Mystery Box with random crypto!

ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት በመቃብር የክርስቶስ በከርሰ መቃብር ሦስት ቀን ሦስት ሌሊ | ትምህርተ አበው

ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት በመቃብር

የክርስቶስ በከርሰ መቃብር ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት የመቆየቱ ነገር እንዴት ነው ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ በሙሉ አቆጣጠሩን ይህን ይመስላል:-

በመጀመሪ ጌታችን ከሦስት ቀን በኋላ እንደሚነሳ የተናገሩ ትንቢቶችን ምሳሌዎችን እና እራሱ በመዋዕለ ስብከቱ ያስተማረውና እንመልከት።

“ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ #ሦስት #ቀንና #ሦስት #ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ #ሦስት #ቀንና #ሦስት #ሌሊት ይኖራል።” — ማቴዎስ 12፥40 “

በኋላም ሁለት ቀርበው፦ ይህ ሰው፦ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አፍርሼ #በሦስት ቀን ልሠራው እችላለሁ ብሎአል አሉ።”— ማቴዎስ 26፥6

“የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም #ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር። ማርቆስ 8፥31


ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት አቆጣጠሩ

ከአርብ 12 ሰዓት በፊት ያለው የመዘጋጃ ቀን ይባላል ይኽም ማለት ስንበት አይደለም ማለት ነው። ጌታ ወደ መቃብር የወረደው አርብ 11ሰዓት ስለሆነ የአርብን ቀንና ሌሊት ጠቅሎሎ ስለሚይዝ እንደ አንድቀን ይቆጠራል። ከአርብ 12 ሰዓት እስከ ቅዳሜ 12 ሰዓት ሁለተኛ ቀን ይሆናል።
ከቅዳሜ 12 ጌታ እስከ ተነሳባት ሊሌት ያለችው እንደ አንድ ሙሉ ቀን ይቆጠራል።

በሌላ አቆጣጠር

አርብ ከጠዋቱ 12 ጀምሮ እስከ 6 ሰዓት ቀን ነበር። አንድ ቀን ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ቀኑ ጨልሞ ነበር።አንድ ቀን አንድ ሌሊት።

ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት እስከ 12ሰዓት ደግሞ ቀን ሆኖል አንድ ቀን ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ጠዋተ 12 ደግሞ አንድ ሌሊት ሁለት ቀን ሁለት ሌሊት ሆነ

የቅዳሜ ቀን እና ሌሊት ሦስት ቀን ሶስት ሌሊት በማለት በቤተክርስቲያን ሊቃውንት ይቆጠራል።


ዕለተ ዓርብ ፈጥሮን ዕለት ዓርብ ያዳነን የድንግል ማርያም ልጅ ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም ያድርሰን።



" ገብረ ሰላም በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ "


ዲ/ን ፍቃዱ ጎንፋ (ዘፍቁረእግዚእ)
ለቀዳም ሥዑር/2014