Get Mystery Box with random crypto!

#የታሪኩ_እርዕስ_ኢምሩ_ከቀብርህ_በላይ #ፀሀፊ_በፎዚያ #ክፍል_ሁለት በእርግጥም እኔም ከአመታት | Lovely😍😘

#የታሪኩ_እርዕስ_ኢምሩ_ከቀብርህ_በላይ
#ፀሀፊ_በፎዚያ
#ክፍል_ሁለት

በእርግጥም እኔም ከአመታት በፊት ከሱ የባስኩ ነበርኩኝ እናም ጓደኞቼ አንድ ቀን በሂወቴ ተሳስቼ የማላዉቀዉ ነገር ተከሰተ ቡሀላ ነዉ ሁሉን እርግፍ አድርጌ የተዉኩት
ያዉ ሁሉም ነገር አዲስ ሲሆንብን በወጣትነት ዘዉ ብለን እንገባና ለመዉጣቱ አንዳንዶቻችን ይከብደናል አንዳንዶቻችን ደሞ ይቀለናል እስቲ እራሴንና ወንድሜን በደንብ ላስተዋዉቃቹ
<<ስሜ አማር ሰኢድ ይባላል አሁን 24 አመቴ ነዉ ትምርት በማርኬቲንግ ተመርቄ ስራ እየፈለኩ ነዉ
<<ወንድሜን ደሞ ሳስተዋዉቃቹ ኢምራን ሰኢድ ይባላል መንትያዬ ነዉ እሱ ትምርት ከአስር ነዉ ያቆመዉ ያዉ ከኔ በፊት ደረሳ ነበር ብዙም የትምርት ቤት ሂወትን አያቀዉም ከሆነ ጊዜ ቡሀላ ግን ባህሪዉ ተበላሽቶ የኔን ቦታ ሲይዝ እኔ ግን በሱ ቦታ ተተካ የተባልኩ ይመስል ወደ ደረሳነት አለም ተቀላቅያለሁ እዉነታዉ ግን አማር የተቀየረበትን ምክንያት አለማወቄ ነዉ።

"የምር አማር ግን ምን ሆኖ ነዉ በአላህ ቆይ ወንድሙን የገደለዉ እሱ ነዉዴ
<እህቴ አማር በጭራሽ ሊገለዉ አይችልም እሱ እንደዚ አይነት ጨካኝ አይደለም
<<የኔ ቆንጆ እህት አንቺን ለዚ ያበቃሽኮ እነዚ የተረገሙ ሁለት ወንድማማቾች ናቸዉ ምነዉ ለምን እንደዚ ትቆረቆሪላቸዋለሽ
<ሀዩ እኔ በሁለቱም አላዝንም ይሄኮ ቀዳቀድር ነዉ ደሞ ጥፋቱ ሁለታችንም እዛ የመገኘታችን ነዉ
<<ሀሲማ አታናጂኝ እንደስምሽ ሁኚ እንጂ ሀሲማ ማለትኮ የተከበረች ነዉ እናም በሱ የተነሳ ክብርሽን አጥተሽ ዛሬም ለሱ ትቆረቆሪያለሽንዴ
<ሀዩዬ እባክሽ በቃ እርሺዉ እኔ ሁሉንም ለአላህ ብዬ ትቼዋለህ አንቺም ተያቸዉ በቃ አሁን ሂወቴን እየመራዉኮ ነዉ እህቴ ለምን በሆነዉ ባልሆነዉ እንጨቃጨቃለን
<<የኔ ቆንጆ ሀሲም እወድሻለሁ እሺ እህቴ ለአንቺ ስል መሞት እንኳንኮ አልፈራም እሺ ሀቢበቲ በቃ እኔ አሁን አንድ ስራ አለብኝ ለእራት ልመለስም ላልመለስም እችላለሁ
<እሺ እህቴ በቃ ደዉይልኝ ኡሚንም ሳሚልኝ እሺ
<<የኔ ቆንጆ እሺ ኢንሻአላህ አንድ ቀን ወደ ቤት ተመልሰሽ ከአባቢ ጋርም ደስተኛ ሂወት እንደምንኖር ተስፋ አለኝ
<ሀዩ
<<ወዬ ሀሲም
<እኔ ለጥፋቴ የተቀጣዉ አይመስልሽም ነዉ ወይስ ከዚ ቡሀላም ሌላ ቅጣት አለኝ
<<የኔ ቆንጆ ደናደሪ በቃ ልሂድ።
ሀሲማን ተሰናብቼ ለጥያቄዋ መልስ ሳልሰጣት ወጣሁ ምክንያቱም እሷ በሂወቷ አበቃ ስትል ሁሌም አዲስ ፈተናና አዳዲስ ችግሮች ይፈራረቁባታል ሀሲማ ማለት ታናሽ እህቴ ናት ከኔ ተደብቃ ኢምራንን ታወራዉ እና ታገኘዉ እንደነበር ጠንቅቄ አዉቃለሁ እሷ ግን እኔ እንደማዉቅ አታዉቅም ቤተሰቦቻችን በጣም ሀይለኞችም ስለሆኑ እኛ ከነሱ እርቀን ወንድማችን ቤት ነዉ የምንኖረዉ እህቴንማ አባቴ በተለይ አይንሽን ለአፈር ብሏታል ምክንያቱም ልታገባ አንድ ወር ሲቀራት ዉጪ አድራ ስለመጣች እናም ከጊዜ ቡሀላ አባቢ ቲኒሽ የተማረ ስለነበር ቀድሞ አስመርምሯት እርጉዝ ስለሆነች ከቤት በጨለማ ነበር የተባረረችዉ ይሄ ሁሉ ደሞ የሟቹ የኢምራን ጣጣ ነዉ እኔም ለበቀል ና ለማሰቃየት ብዬ ከሱ ጋር በሆነ አጋጣሚ ኒካህ አሰርኩ ነገር ግን እኔ ሳላሰቃየዉ ሞት ቀደመዉ እንጂማ እሱን አቅጄለት ነበር አሁን እቅዴን ጨርሼ ለወንድሙ አማር አዘዋዉሬአለዉ ያዉ ለመቀጣጫነት ያህል

"አማሬ አንተ አማር በቃ እኔ ልጄን ካጣሁ ቡሀላ ከሱ ዉጪ የሚያባሽረኝ ሰዉ ልጣንዴ የኔ ልጅ
<<ዉይ ኡሚዬ ሀቂቃ እመጣለሁ እያልኩኝኮ እረሳዉት
< በል ና ዉጣ
<<እሺ ኡሚዬ
<እኔ ምለዉ ሀያቴ መጥታኮ ብዙም ሳትቀመጥ ነዉ የወጣችዉ አገኘሀት አይደል
<<አዎ አጊንቻታለሁ ያዉ ግን የወንድሜ ሀዘን በጣም ጎድቷታል እናም የምትናገረዉን እራሱ መቆጣጠር እየከበዳት ነዉ
<ምነዉ አማሬ የተናገረችዉ ነገር ነበርንዴ
<<አይ ኡሚ ብቻዋን ተክዛ ስላየዋት ነዉ። ኡሚ ቆይ አንድ ጊዜ ስልክ ላዉራ አዲስ ቁጥር ነዉ።
<እሺ ልጄ ብለዉ ተሰናብተዉ ከክፍሉ ወጡለት

<<ኡሚ አንዴ ወጥቼ እመለሳለሁ መጣሁ ሀዩ ደዉላልኝ ነዉ አንዴ አጊንቻት መጣሁ.....

#ክፍል_ሶስት_ይቀጥላል......

#ይህ_ታሪክ_እንዲለቀቅ_Like #ሼር_ያድርጉ_ታሪኩን

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ


ይቀላቀሉን ይቀላቀሉን
@fetiium