Get Mystery Box with random crypto!

​ አጭር የፍቅር ታሪክ... ሳሙኤል አንድ ጊዜ የሚፈልጋት አይነት ሴት ወደ ህይወቱ | Lovely😍😘

​ አጭር የፍቅር ታሪክ...


ሳሙኤል አንድ ጊዜ የሚፈልጋት አይነት ሴት ወደ ህይወቱ መጣች..ስሟ ማርታ ይባላል፡፡ሰዉነቷ የሞዴል፣ቆዳዋu ደግሞ እንደ ጠዋት ወገግታ የሚያምር ዉብ ነበር፡፡

በጣም ቆንጆና ማራኪ ስለነበረች ፍቅረኛዉ ቢያደርጋት ጓደኞቹ ሁሉ ምነዉ እሱን ባደረገኝ ብለዉ እንደሚቀኑ ገና ከአሁኑ በአእምሮዉ ስሎታል፡፡

ከማርታ ጋር ግንኙነታቸዉን ካጠበቀዉ በኋላ የፍቅር ጥያቄ ያቀርብላታል፡፡እሺታዋን ትሰጠዋለች፡፡በጣም ደስ ይለዋል ግንኙነታቸዉም እየጠበቀ ይሄዳል፡፡

አብረዉ ረጅም ጊዜያትን ካሳለፉ በኋላ ሳሚ አንድ አሳዛኝ ክስተት ልቡ እያቀበለዉ እንደነበር ቆይቶም ቢሆን ይገባዋል፡፡ማርታ ጋር ፍቅር ሊይዘዉ አልቻለም ወይም አላፈቀራትም!

የሚወደዉ ነገር ከሷ ጋር አብሮ መሆኑና ጓደኞቹ ለእሱ ያላቸዉ አድናቆትና ትልቅ ቦታ ነዉ፡፡
ሌላ ተጨማሪ አንድ ትልቅ ችግር ደግሞ አለ፤ማርታ ከፍቅር ዉጪ ለምንም ነገር ፍላጎት የሌላት አፍቃሪ ሴት ናት፡፡

ገና ከልጅነቷ በጣም የሚወዳት ልኡል ሊያገባ ሲወስዳትና እስከመጨረሻዉ አብረዉ በፍቅር ሲከንፉ ስንት ጊዜ በህልሟ አይታለች፡፡

ሳሚ አሁን ግራ ገብቶታል፤ማርታን ከተዋት ጓደኞቹ የሚሰጡት ክብርና ዝና አፈር ሊበላ ነዉ፡፡ለዛ ደግሞ ዝግጁ ስላልሆነ አንድ ነገር ያደርጋል፤

እራሱን በማስገደድ በግድ ማርታን መዉደድ! ይህንን ግዳጅ ለማድረግ ካሰበበት ቀን ጀምሮ በማርታ ፍቅር እንደጦዘ ሰዉ ሆኖ ድራማዉን መተወኑን ተያያዘዉ፡፡በየጊዜዉ ትወናዉን እያሻሻለ ምርጥ አፍቃሪ መሆኑን ለአለም አሳየ፡፡

ምስኪኗ ማርታ በእዉነተኛ ፍቅር ልቧ ተነደለ!በስተመጨረሻ ስታልመዉ የነበረዉን ልዑል እንዳገኘችዉና ትንቢቱ እንደተፈፀም ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ አላደረባትም፡፡

ሳሚ ልክ በሷ ስፌት የተሰፋ የፍቅር መላእክ እስኪመስላት ድረስ ወደደችዉ…ከንፍፍፍ አለች!
ከአምስት ወር በኋላ ሳሚ ልቡን የምታቀልጠዉን ሴት ተዋወቀ! ስሟ ሰላም ይባላል፡፡ ገና ሰላምን ሲያያት በፍቅር እንደወደቀ ገብቶታል፡፡

የአይን ፍቅር ተዋናዩን ሰዉዬ ጉድ አደረገዉ፡፡አሁን ሌላ ቦንብ አለ…አዲሱ ፍቅረኛዉን ከማያፈቅራት ማርታ ጋር እንዴት አድርጎ ያስኪደዉ…ግራ ገባዉ፡፡

ነገሮች በቀላሉ እንደማይፈቱ ያዉቀዋል፤የቻለዉን ያህል ሰላምን ለመርሳት ቢሞክርም እሷ ግን የልቡን ካርታ እየወረሰች መጥታለች፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ ለማርታ እንደሚያፈቅራት የፎገረበትን እነዛን ሁሉ የዉሸት ጊዜያት አሰባቸዉና ዘገነነዉ፡፡

ነገሮችን ለሁለት ወር ያህል አምቆ ለማቆየት ቢሞክርም ከዛ በላይ ግን መኖር አቅቶታል፡፡በመጨረሻም ለማርታ እዉነቱን ዘረገፈዉ፤

ብዙ ለማፍቀር ቢሞክርም እሷን ማፍቀር እንዳልቻለና ያ ሁሉ ሲዘላብደዉ የነበረዉ ነገር ድራማ እንደነበር ነገራ…እሱ ብቻ ሳይሆን ከልቡ የሚያፈቅራትን የሚሳሳላት ፍቅረኛ ማግኘቱንና ከዚህ በኋላ አብረዉ መቀጠል እንደማይችሉ እየተንተባተበም ቢሆን ቃል በቃል ተነፈሳት፡፡

ማርታ አለም ተገለበጠባት ሁሉ ነገሯን የሰጠችዉ ሰዉ እንደማንጎ ልጣጭ የትም ጥሏት መሄዱን ስትሰማ ዉስጧ ሚሊየን ጊዜ ደማ!

ከሶስት የድብርትና የሀዘን ሳምንታት በኋላ ማርታ ሁሉን ረስታ መደፊት መሄድ እንዳለባት ቆረጠች፡፡ግን ከዛ በኋላ ወንድ የተባለ ፍጡር ላይ በቀሏን በሚገባ ልትወጣና አደገኛ የፍቅር ተዋናይ ልትሆን በራሷ ፊት ቃል ገባች፡፡

➺➺➺➺➺➺share
➸➸➸➸➸➸share @fetiium
@Umnaaaa