Get Mystery Box with random crypto!

ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ የሠላም አባት! የኢ/እ/ጉ/ጠ/ም ዋና ፕሬዝደንት ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱ | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ የሠላም አባት!

የኢ/እ/ጉ/ጠ/ም ዋና ፕሬዝደንት ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤን በበላይነት አስታረቁ።


ታህሳስ 25/2015 ማክሰኞ

ከሰሞኑ በተፈጠረዉ ወቅታዊ ጉዳይ ማለትም ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር በተያያዘ አስተምህሮቱ የሚያጠለሽና መከባበርን የሚያደፈርስ ስብከቶች ተፈጽመዉብኛል በማለት ለቀረበዉ አቤቱታ ጉባዔዉ አስፈላጊ እርምጃ ባለመውሰዱ ምክንያት ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመውጣት ማሳሰባቸዉን ተከትሎ የተፈጠረዉን ጉዳይ እንደአባት ኃላፊነት በመውሰድ፣ እርቅና ሠላም እንዲሰፍን የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤ/ም ዋና ፕሬዝደንት የሆኑት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ድርሻቸዉ ከፍ ያለ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ከጤናቸዉ አኳያ ከቦታ ወደቦታ መዘዋወር ስለማይችሉ በእሳቸዉ ቢሮ ውይይት የተካሄደ ሲሆን  የጋራ ውይይቱን በመምራትና በማስታረቅ በሠላም፣ በፍቅርና በመከባበር እንዲሰምር ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ የአባትነት ሚናቸዉን ተወጥተዋል።

የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤ/ም ዋና ፕሬዝደንት ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባላትንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችን በማስታረቅና በጉባዔዉ እንዲቀጥሉ በማሳለጥ ወደ ፊትም ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ስምምነት ላይ እንዲደርሱ አድርገዋል።


ሙጂብ አሚኖ



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia