Get Mystery Box with random crypto!

ኢስላሚክ ባንክ እና ከወለድ ነፃ መስኮት አሰራራቸው አንድ ነው በሚል በወለድ ባንክ ገንዘብ ማስቀመ | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

ኢስላሚክ ባንክ እና ከወለድ ነፃ መስኮት አሰራራቸው አንድ ነው በሚል በወለድ ባንክ ገንዘብ ማስቀመጥ አልተፈቀደም።

ምክንያቱም የሪባ ባንኮች ገንዘቡን አላህን ለማመፅ ይጠቀሙበታል። በእነዚህ ባንኮች ገንዘቡን የሚያስቀምጥ ደግሞ የሪባ ሰዎችን ጉልበት እያፈረጠመ ነው።

አላህ ደግሞ «በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ።» በማለት ከወንጀለኞች ጋር መተባበርን ከልክሏል።

በአንፃሩ አንድ ሰው ኢስላሚክ ባንክ ከተጠቀመ የሪባ ሰዎችን እየተዋጋ ነውና የአላህን ሃይማኖት እየረዳ ነው።

አንዳንድ ሰዎች ኢስላሚክ ባንክም ሆኑ የሪባዎቹ ለግላቸው ጥቅም የሚነገዱ ከሆነ ምን ልዩነት አለው? ይላሉ።

ልዩነት አለው፦

አንደኛ አላህ ንግድን አልከለከለም። ሪባን ግን ከልክሏል። ስለዚህ ሪባን እንደ ዋና የገቢ ምንጩ ከያዘ አካል ጋር ካለሪባም ቢሆን መገበያየት አልተፈቀደም።

ሁለተኛ ኢስላሚክ ባንክ ሰዎችን ከሪባ የሚጠብቅ በመሆኑ ጥቅሙ ለባንኩ ባለቤቶች ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ሙስሊም ጭምር ነው።

አንድ ሰው ከወንጀል የጠበቀውን ጉዳይ አልጠቀመኝም ብሎ የሚያስብ ከሆነ ደግሞ የኢማን ትርጉሙ አልገባውም። ወይም ሰው ለምን አገኘ የሚል ቅናተኛ ነው።

በአገራችን ወለድ አልባ መስኮት ይፈቀዳል እያሉ የሪባ ባንኮችን ገንዘብ እንዲያካብቱ ምክንያት የሆኑ ዳዒዎችና ዑለማዎች አሉ። ይህ ጉዳይ ኢስላሚክ ባንክ ከመምጣቱ በፊት ከሆነ ችግር የለውም። ባንኮቹ ከተመሰረቱ በኋላ ከሆነ ግን ወለድ አልባ መስኮትን ማበረታታት ኢስላማዊ ባንኮችን ማዳከም ነውና ከዚህ ስህተታቸው መታረም አለባቸው። ኢስላሚክ ባንክ እያለ ወለድ አልባ መስኮትን የሚፈቅድ አንዳችም ማስረጃ የለም። ካልሆነ አላህ ይጠይቃቸዋል።

ሰል ማን




https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia