Get Mystery Box with random crypto!

ነሲሐ ቲቪ ስርጭት እስኪቋረጥ ድረስ መድረሱ በራሳችን ልናፍር ይገባል! ነሲሓ ቲቪን መርዳት የውዴ | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

ነሲሐ ቲቪ ስርጭት እስኪቋረጥ ድረስ መድረሱ በራሳችን ልናፍር ይገባል!

ነሲሓ ቲቪን መርዳት የውዴታ ግዴታች ነው!

አቡ ዳውድ ኡስማን

ነሲሐ ቲቪ ስርጭቱን ለህዝበ ሙስሊሙ ማድረስ ከጀመረባቸው ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ኡማን ምን ያህል እየጠቀመ ስለመሆኑ ሁሉም በየቤቱ የሚመስክረው ጉዳይ ነው፡፡

"ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም" በሚል መርህ ኢስላማዊ አስተምህሮዎችን በሁሉም ዘርፎች ለህዝበ ሙስሊሙ ሲያቀርብ የቆየ ቢሆንም በአቅም ውስንነት ምክንያት ባለፈው ከኢትዮ ሳት አሁን ደግሞ ከናይል ሳትም ስርጭቱ ተቋርጧል::

ይህ በየቤታችን ተወዳጅ እየሆነ የመጣው የቲቪ ቻናል አስተማሪ እና ጣፋጭ ትምህርቶቹን ለህዝበ ሙስሊሙ ማድረሱን እንዲቀጥል የሁላችንም እገዛ በአሁኑ ወቅት ያስፈልገዋል፡፡

እንደሌሎቹ የሙስሊሙ ሚዲያዎች ይህም ቲቪ ለትርፍ ያልተቋቋመ የዳዕዋ ጣብያ በመሆኑ ትምህርቶቹን በሳተላይት በየቤታችን እንዲያደርስ የኛ የገንዘብ ድጋፍ ወሳኝ ነው፡፡

ዛሬ ላይ አቅማችን በፈቀደው መልኩ ድጋፍ ብናደርግ በቲቪው በሚቀርበው መልካም ትምህርት እና በሚገኘው አጅር ሁሉ ተቋዳሽ እንደምንሆን እናስተውል፡፡

ትንሽ ገንዘብ ሰጥተን በየቀኑ ብዙ አጅር የሚያሸምተን በዚህ መልካም ስራ ላይ እንሳተፍ፡፡

የሙስሊሙ ሚዲያዎች ሁሌም በህዝብ ድጋፍ ብቻ ተንጠልጥለው መቆየት የለባቸውም፡፡ በዘላቂነት እራሳቸውን የሚችሉብት ሁኔታ ሊፈጠርላቸው ይገባል፡፡

ነሲሐ ቲቪንም እራሱን ችሎ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም በሚል የጀመረውን የዳዕዋ ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ዛሬ ላይ የሁላችንም ድጋፍ ይሻል፡፡

ሙስሊሙ ማህበረሰብ ካለው አቅም አንፃር ጥቂት ሙስሊሞች ብቻ የቲቪውን ወጪ መሸፈን ይቻል ነበር፡፡ ሁሉም በዚህ መልካም ስራ ላይ ተሳትፎ ያደርግ ዘንድ ይህ እድል ለሁላችንም መጥቶልናል እና የበኩላችንን እንወጣ::

አላህ አቅም የሰጣችሁ ወንድም እና እህቶች የካፊ*ር ሚዲያዎች በግለሰብ ስም ሳይቀር እየተከፈተ ባለበት በዚህ ወቅት ሙስሊሙ ያሉት ጥቂት ሚዲያዎች በአቅም እጥረት ምክንያት መዘጋት እንደሌለባቸው አምናችሁ አላህ በሰጣችሁ ገንዘብ በመለገስ የማይቋረጥ አጅር ሸምቱ!

ሰዎችን ወደ አላህ መንገድ በጥበብ ለመጣራት እውቀቱ ባይኖርህ እንኳን እውቀት ያላቸው ሰዎች ወደ አላህ ሰዎችን እንዲጣሩ አላህ በሰጠህ ገንዘብ አግዛቸው፡፡ አንተ በገንዘብህ ሌሎች ደግሞ በእውቀታቸው ህዝቦችን ወደ አላህ መንገድ እንዲመጡ የበኩልህን ተወጣ!

ድጋፍ ለማድረግ ለምትፈልጉ ወንድም እና እህቶች በተከታዩ የባንክ አካውንት ድጋፍ በማድረግ ለነሲሓ ቲቪ ቀጣይነት አስተዋፅኦ ያበርክቱ
***
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የሂሳብ ቁጥር 444

ነሲሓ ቲቪ... ኢስላማዊ ዕውቀት ለሁሉም!

Abu dawd osman



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia