Get Mystery Box with random crypto!

የነዳጅ ዋጋ ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ም | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የነዳጅ ዋጋ

ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

ቤንዚን በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም
ነጭ ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም
ኬሮሲን በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም
ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 53 ብር ከ10 ሳንቲም
ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር ከ37 ሳንቲም
የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 98 ብር ከ83 መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከላይ የተገለጸው የቤንዚን ፣ የኬሮሲን እና የነጭ ዋጋ ላይ ለህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ወይም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች 15 በመቶ በመንግስት እንዲደጎሙና ቀሪውን 10 በመቶ እንዲከፍሉ በማድረግ የድጎማ መጠኑን በቴሌ ብር ተመላሽ እንዲሆንላቸው ይደረጋል ተብሏል።

የተደረገው የዋጋ ማስተካከያ የተደረገባቸው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዝርዝር ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ሁሉ ተግባራዊ ይሆናል።

ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

@fethababora