Get Mystery Box with random crypto!

እሳቸው ግን በሠርጉ ሌሊት ከጫጉላ ቤት ጠፍተው በርሃ ገቡ:: ከዚያም በቅዱስ መልአክ መሪነት ሃገረ | የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት መዝሙር እና ኪነ-ጥበብ ክፍል(የፈ/ጥ/ሰ/ት/ቤት ደብረ ዘይት)

እሳቸው ግን በሠርጉ ሌሊት ከጫጉላ ቤት ጠፍተው በርሃ ገቡ:: ከዚያም በቅዱስ መልአክ መሪነት ሃገረ ምሑር ደረሱ:: በቦታውም ጣዖትን ሰባብረው: ተአምራትንም አድርገው: ሕዝቡን ወደ ክርስትና መለሱ:: መስፍኑ አውጊት ግን ተፈታተናቸው: አሠራቸው: አሥራባቸው::

በጦር እወጋለሁ ሲል ግን መሬት ተከፍታ ከነ ተከታዮቹ ውጣዋለች:: ከ5 ዓመታት በኋላ ግን ማልደው: ከሰጠመበት አውጥተው አጥምቀውታል:: ቀጥለውም ምድረ ጉራጌ ወርደው: ሕዝቡን አሳምነው አጥምቀዋል::

የአዳልን ሕዝብና ንጉሡን አብደልማልን አስተምረው ያጠመቁም እርሳቸው ናቸው:: ድል አሰግድ የሚባለውን መስፍንም ያሳምኑ ዘንድ ጠንቅዋዮቹን ድል አድርገው አጥፍተዋል::

ጻድቁ ዜና ማርቆስ ከዚህ ሐዋርያዊ ሥራቸው በተጨማሪ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ምንኩስናን ከተቀበሉባት ቀን ጀምረው በጾም: በጸሎትና በሰጊድ ኑረዋል:: ፀሐይን በምድረ ጉራጌ እስከ ማቆም ደርሰውም ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል::

አእላፍ ደቀ መዛሙርትን ሲያፈሩ 200 አንበሶች በቀኝ: 200 ነብሮች በግራ ይከተሏቸው ነበር:: ደብረ ብሥራትን ጨምሮም ገዳማትን አንጸዋል:: በመጨረሻም የምሕረት ቃል ኪዳንን ከፈጣሪ ዘንድ ተቀብለው ታኅሣሥ ሦስት ቀን በ140 ዓመታቸው ዐርፈዋል::

††† የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን::

††† ታኅሣሥ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም
2.ብጹዓን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ካህናት ዘካርያስና ስምዖን
4.ቅዱስ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት
5.አቡነ ዜና ማርቆስ ጻድቅ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ጻድቅ (ዘደብረ በንኮል)
2.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
3.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)

††† "ድንግል ሆይ! አንገታቸውን እንደሚያረዝሙ እንደ እብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም:: በቅድስናና በንጽሕና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ::
ድንግል ሆይ! ምድራዊ ሕብስትን የተመገብሽ አይደለም:: ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ሕብስትን እንጂ::
ድንግል ሆይ! ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም:: ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን እንጂ::" †††
(ቅዳሴ ማርያም)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††