Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና! ታላቁ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም በታጠቁ ኃይሎች እየታመሰ ይገኛል ፡፡ ታኅሳስ | የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት መዝሙር እና ኪነ-ጥበብ ክፍል(የፈ/ጥ/ሰ/ት/ቤት ደብረ ዘይት)

ሰበር ዜና!

ታላቁ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም በታጠቁ ኃይሎች እየታመሰ ይገኛል ፡፡

ታኅሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

የበርካታ መናንያን መኖሪያ ታላቁ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም በታጠቁ ኃይሎች እየታመሰ ይገኛል ፡፡ ማምሻው የታጠቁ ኃይሎች በሁሉም አቅጣጫ ወደ ገዳሙ ሰብረው በመግባ መነኮሳትን በማገት ገዳሙን እያመሱት ይገኛል ፡፡

ሚዲያችን የሚመለከታቸውን አካላት ቦታው ድረስ በመደወል እየደረሰባቸው የሚገኘውን እንግልት ተረድተናል "ከገዳሙ የጥበቃ ኃይሎች የሚገኙትን መሣሪያዎች በከበባ ነጥቀዋል ፡ ገዳሙን በሁሉም አቅጣጫ በመግባት እያስጨነቁ ይገኛሉ ሦስት አገልጋዮችን አግተዋቸዋል ድረሱል ድረሱልን" የሚል ድምፅን አሰምተዋል ሲል ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘግቧል።
(#FTM)