Get Mystery Box with random crypto!

ሁላችን የምንሳተፍበት የበረከት መንፈሳዊ ጉዞ የሰማዕቱን የቅዱስ መርቆሬዎሰን ህንፃ ቤተክርስቲያ | ሐረር ፈለገ ሕይወት ሰ/ት/ቤት

ሁላችን የምንሳተፍበት የበረከት መንፈሳዊ ጉዞ
የሰማዕቱን የቅዱስ መርቆሬዎሰን ህንፃ ቤተክርስቲያን በአዲስ መተዋበ እና ባማረ መልኩ በሀገረ ስብከታችን የሰንበት ት/ት ቤቶች አንድነት አስተባባሪነት ምዕመናንን በማስተባበር ለአካባቢው ምዕመን ሰርተን ለማስረከብ እንደ እግዚአብሔር ቸርነት በሂደት ላይ እንገኛለን የፊታችን ግንቦት 07/2014 ዓ.ም ወደ አካባቢው መንፈሳዊ ጉዞ በማዘጋጀት
1.ታቦተ ሕጉን ከነባሩ ቤተ መቅደስ ወደ መቃኞ ለማኖር
2. አዲስ ለሚሰራው ቤተክርስቲያንም የመሰረት ድንጋይ ለማስቀመጥ
+ክቡራን አባቶች ቆሞሳትን
++ አገልጋይ ካህናት እና ዲያቆናትን
++ የሰንበት ት/ት ዘማሪያንን
++ምዕመናንን ጭምር ያሳተፈ ልዪ መንፈሳዊ ጉዞ ስለተዘጋጀ ሁላችን ላልሰሙት በማሰማት የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ የክርስትና ግዴታችንን እንድንወጣ በሰማዕቱ ስም ጥሪ እናቀርባለን ::
ቤተ-ክርስቲያኑ አሁን ያለበት ሁኔታ
ከ80 ዓመት በላይ የቆየ ከመሆኑ የተነሳ
* ግድግዳው በመሰነጣጠቅ እና በመፍረስ ላይ ይገኛል
** ጣራው ከመበሳሳቱ የተነሳ ዝናብ በማስገባት
** በር እና መስኮት በቂ ጥንካሬ አለመኖራቸው
** በአካባቢው ያሉ ምዕመናን በቁጥር በገቢም አነስተኛ ናቸው
እኚን እና የመሳሳሉት አይነተኛ ችግሮች በአካባቢው ላይ የሚስተዋሉ ናቸው ::
አላማችን ህንፃ ቤተክርስቲያንን ገንብተን ህንፃ ሥላሴን መስራት ነው በተጨማሪም የቤተክርስቲያኗን ይዞታ ማስጠበቅ ለትውልድም ማስተላለፍ ነውና ሁላችን በእግዚአብሔር ስም የተቻለንን ተሳትፎ እንድናደርግ ጥሪ እናቀርባለን !!!!!!
በጉዞው መሳተፍ ያልቻላችሁ ክርስቲያኖች
በገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ
1000450981854
ንግድ ባንክ ሐረር ዋናው ቅርንጫፍ
በሀሳብ እና በሞያ ድጋፍ ማድረግ ለምትሹ 09 20 89 28 64/ ዲ.ን ወንዶሰን/
09 12 73 86 85 /አንተነህ/
ልዑል እግዚአብሔር በቸርነት አይለየን !!!!
አሜን አሜን አሜን!!!!!!!