Get Mystery Box with random crypto!

በከመ ምህረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ ከአስሩ ድሪም ድንገት ቢጠፋባት ድሪሟን ፍ | ነጌሌ አርሲ ደብረ ልዳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ፈለገ-ገነት ሰንበት ትምህርት ቤት(FelegeGenet Sunday School)

በከመ ምህረትከ አምላክነ
ወአኮ በከመ አበሳነ

ከአስሩ ድሪም ድንገት ቢጠፋባት
ድሪሟን ፍለጋ ሴቲቱ ነነሳች
ቤቷን ስታጸዳ አብርታ መብራቷን
ከቆሻሼ መሀል አየችው ድሪሟን

ያ ድሪም እኔ ነኝ በቃል ማልገኝ
በቤትህ ውስጥ ሆኜ በቤት ማታውቀኝ
ከቆሻሻ ሠሀል ከምታገኛቸው
አገልጋዮች እኔ ነኝ ዋነኛው

በከመ ምህረትከ አምላክነ
ወአኮ በከመ አበሳነ

የሰወከውን ቃል በህይወቱ ነዋሪ
የጠፋው እርሱ ነው ሞልቷል ተናጋሪ
በክፍ ስራዮ በኔ ተነቅፈሃል
የስም ብቻ አገልጋይ መች ያስደስትሃል

ቅርብ ነው አንደበቴ ልቤ ግን የሸሸ
ማንነቴ ባዶ በቃል ያልታሸ
ዛሬ አስተካክለኝ ልታነፅ በቃልህ
በኔ አይሰደቡ ቅን አገልጋዮችህ

ሐገሪቱ ረስታ መገሸብኘቷን ወራት
እንባህን አፈሰሰህ ለሷ አለቀስክላት
ዛሬ ብትመጣ በልቤ ከተማ
አዝነ ታለቅሳለህ በኔ ምግባርማ

በመቅደስ መሃል ድፍረቴ የበዛ
ልቤ ለዓለም እንጂ ላንተ ያልተገዛ
የስም ብቻ አገልጋይ መሆኔን ታውቃለህ
ድሮስ ከኔ አይነቱ ምንስ ታገኛለህ

የቃየል መስዋዕት ከመቅደስ ገብቶ
አንድነት ተረስቶ ሁሉ ተለያይቶ
እንክርዳዱን መስዋዕት ቁራ በትኖታል
ፍቅር አልባ መስዋዕት መች ያስደስትሃል

ይቁም በመቅደስህ መሸጥ መለወጡ
አፍኒንና ፊንሃስ በመቅደስህ ይውጡ
ሳሙኤልን መሰል ቅን አገልጋዮችህ
በመቅደስ ይብዙ ተናገር ይበሉህ

በከመ ምህረትከ አምላክነ
ወአኮ በከመ አበሳነ
✤✤✤✤✤✤✤
በመዝሙር ክፍሉ በኩል የተለቀቀ ሲሆን አገልጋዮች እራሳችንን የምንመረምርበትና ትንሣኤ ልቦናና ትንሣኤ ህሊናችንን አስመልሰን በንቃትና በትህትና በፍርሃተ እግዚአብሔር እናገለግል ዘንድ የሚያደርገን ስለሆን ምክርም ተግሳፅም ይሁነን✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢

አቤቱ አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይሁን/3/