2022-05-05 17:04:56
ችግር ያሳድጋል!
ችግራችሁን ተጋፈጡ እንጅ አትሽሹ!
☞ ኑሮ በየቀኑ የምንወጣው ተራራ ነው ፡፡ አንዱን ጨርሰን ስንደሰት ሌላኛው ይደቀናል ፡፡ ሌላኛውን ስንወጣ የባሰው ደግሞ ይጠብቅናል ፡፡ የማያቋርጥ ስቃይ አለብን ፡፡ ስቃዩ ግን ጥሩ ነው ፡፡ ትክክለኛ አቅማችን የሚወጣው ከትክክለኛ ፈተና ጋር ስንታገል ነው ፡፡
☞ ብዙ ሰው ከፊቱ ያለውን ተራራ ግዝፈት እንጂ በውስጡ ያለውን የፈጣሪን ጉልበት አያውቅም ፡፡ ተራራው ከፊትለፊቱ ሲደቀን የሚወጣበትን መንገድ ከመፈለግ ይልቅ ማማረርን ይመርጣል ፡፡ ምክንያቱም ማማረር ቀላል ነዋ ፡፡
☞ ማለቃቀሱን ማንም ያውቅበታል ፡፡ ወደ ተራራው ጫፍ የሚወስደውን መንገድ ማግኘት ግን ከባድ ነው ፡፡ ይህ የጥቂት ጀግና ሰዎች ስራ ነው ፡፡ ላብ ፣ ደምና እንባ ማፍሰስን ይጠይቃል ፡፡ ብዙ ሰዎች ደግሞ ይህን ማድረግ አይፈልጉም ፡፡ ፈሪና ሰነፎች ናቸው ፡፡ በራሳቸው ጉልበት ፤ በፈጣሪያቸውም ሐይል እምነት የላቸውም ፡፡ ምኞታቸው ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ እንዲሆን ነው ፡፡ ህይወት ደግሞ ተራራ በተራራ እንጂ አልጋ በአልጋ አይደለም ፡፡
☞ ዓለም አሁን ካለችበት ከፍታ የደረሰችው በችግር ነው ፡፡ ችግር ባይኖር ? ሰዎች ዛሬም ድረስ በዋሻ ውስጥ ነበርን ፡፡ መብራት ፣ መኪና ፣ እርሻ ፣ ፕሌን ፣ ኢንተርኔት ፣ ስልክ ፣ ኮምፒውተር ፣ ቤትና ሁሉም ለሰው ልጆች ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች የተወለዱት በችግር ምክንያት ነው ፡፡
☞ ሰዎች ችግራቸውን ለማሸነፍ ሲታገሉ ዛሬ ፍጹም ልዩ የሆነ አለም ፈጥረዋል ፡፡ ታዲያ ምስጋና ለአቶ ችግር አይገባም ትላላችሁ ? ከፊት ለፊታችሁ ያለው ተራራ ምንድን ነው ? ችግራችሁ ምንድን ነው ? ገንዘብ ማጣት? ስራ አጥነት ? የተበላሸ ትዳር ? ስደት ? በሽታ ? በራስ መተማመን ማጣት ? ሱስ ? ምንድን ነው ?
☞ ችግራችሁን የምትመለከቱትስ እንዴት ነው ? ተራራችሁን የምታዩት እንዴት ነው ? ሊያሳድጋችሁ እንደመጣ ስጦታ ? ወይስ ሊያስቆማችሁ እንደመጣ ፈተና ? ይህ የምርጫ ጉዳይ ነው ፡፡ ብዙ ሰው ችግሩን እንደ ጠላት ይመለከታል ፡፡ ችግራችሁን እንደ ወዳጅ አድርጋችሁ ካያችሁ ግን እናንተ ትክክለኛ ጀግና ናችሁ ፡፡
☞ እሱን ለማሸነፍት ስታነቡ ፣ ሰው ስታማክሩ ፣ ሞያ ስትለማመዱ ፣ ስትነግዱ ፣ ገንዘብ ስትቆጥቡ ፣ ጸሎት ስታደርጉ ፍጹም ሌላ ሰው ትሆናላችሁ ፡፡ ሌሎች ከታች ሆነው ሲያማርሩ እናንተ ከተራራው ጫፍ ትደርሳላችሁ ፡፡ ከአናቱ ሆናችሁ ንፁህ አየር ትምጋላችሁ ፡፡በከፍታው ያለውን ቪውም enjoy ታደርጋላችሁ ፡፡ ሌላ ችግር ሲጋረጥባችሁም አትደናገሩም ፡፡ ሌላ መፍትሄ ፈልጋችሁ ታሸንፉታላችሁ ፡፡
@enkopawiyan
@enkopawiyan
@betina21
https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
81 viewsBetina, 14:04