Get Mystery Box with random crypto!

#መተኛት እወዳለሁ እንቅልፋም ናት ይሉኛል ።............. የምርም መተኛት እወዳለሁ ደግ | HOT LOVE 🥰

#መተኛት እወዳለሁ

እንቅልፋም ናት ይሉኛል ።.............
የምርም መተኛት እወዳለሁ ደግሞም ምክንያት አለኝ ምከንያቴም እሱ ነው ህልሜ ውስጥ እሱ አለ.....
ከተዋወቅንበት እስከ አሁን ያሉትን ጥሩ ቀናት መጥፎ ትዝታዎችም ጭምር በየተራ ይመጣሉ ........

መጀመርያ እሱ ነው ቀርቦ ፍቅር ያስያዘኝ ከዛማ በቃ... ማቆም ወደማልችልበት ቦታ ብቻዬን መሄድ ጀመርኩ ግን የማይረሱ ውብ ጊዜያት አሉን.....

ሁሉንም በምናቤ እስላቸውና እደሠታለሁ ..ብዙም ሳልቆይ ንትርኮችቻችንን አስታውስና ዛሬ እንደሆነ ያህል እናደዳለሁ ..ስለ ተጣላንበት ነገር ሳስብ እበግናለሁ ...........

በቃ ሀሳብ ነው ............እሱን መሳም ማቀፍ ማየት አይኔን በጨፈንኩ ቁጥር እየተመላለስኩ አስበዋለሁ ሲስቅ እነዛ ጥርሶቹ ሲጫወት የሚያምረውን ፊቱን ባይምሮዬ እስልና እንደቀልድ ሌሊቱ ያልፍና በብርሀን ይተካል ምርጫ የለኝም ሰው ሲነሳ እኔ እተኛለሁ..

እ እና እንቅልፋም ነኝ ??...