Get Mystery Box with random crypto!

ሠላም ውድ ተመራቂ ተማሪዎች በመጀመሪያ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን ።አንድ ሁለት እ | Gondar fasil UOG (ኢንጂነሮቹ) ቻናል❤️

ሠላም ውድ ተመራቂ ተማሪዎች
በመጀመሪያ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን ።አንድ ሁለት እያልን #5ዓመታትን ቆጥረን አዲስ የህይወት ምዕራፍን ለመጀመር በጣም ጥቂት ቀናት ቀርተውናል እኛም ይህንን አስመልክተን #50ኛ ቀናችንን በጣም በደማቅ እና በማይረሳ መልኩ ለማክበር
#ሐምሌ 10/2014 ቀነ ቀጠሮ ይዘን ዝግጅታችንን ጨርሰናል።
በዚህ ልዩ ቀን
በአይነቱ እጅግ ልዩ የሆነ የእራት ግብዣ
የቀይ ምንጣፍ የፎቶ ፕሮግራም
ተወዳጆቹ የመድረክ ላይ ፕሮግራሞች
ልዩ ልዩ አዝናኝ እና ፈታኝ ውድድሮች
የምስጋና ፕሮግራም
እንዲሁም አንድ ተብሎ ከጊቢ ስንወጣ ጀምሮ እስከ ፕሮግራማችን ፍጻሜ ድረስ ሁሉም ነገር በ ፕሮፌሽናል ካሜራማን የሚቀረጽ ሲሆን ይሄ በህይወት አንድ ግዜ የሚከበር በዓል እና ልዩ ታሪክ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በሁላችንም እጅ የሚገባ ይሆናል
በተጨማሪም ወንዶቹ በገራሚ ሱፍ ቂቅ ብለን ሴቶቹ ደግሞ በልዩ የራት ልብስ አምሮባችሁ የ ትራንስፖርት ሁኔታ ሊያሳስበን አይገባም ምክንያቱም ምቾታችን ሳይጓደል አንከብክበው ከግቢያችን በር አንስቶ እስከመዳረሻችን ድረስ እንዲሁም ፕሮግራማችን ሲያልቅ ወደጊቢ የሚመልሱን የትራንስፖርት አማራጮች ተዘጋጅተዋል
በአጠቃላይ ይሄ ቀረሽ የማይባል ልዩ የ50ኛ ቀን በዓል ዝግጅቱን ጨርሶ የእኛን መምጣት እና የቀኑን መድረስ እየተጠባበቀ ይገኛል
በመሆኑም በዚህ ልዩ እና በህይወት አንድ ግዜ በሚደረግ ታሪካዊ ቀን ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችዋል ።
በዓሉ የሚከበርበት ቦታ
ሃይሌ ሪዞርት(HAILE RESORT)
ይህን ልዩ ቀን ለማክበር የሚያስፈልገን የብር መጠን የትራንስፖርት ወጪን ጨምሮ
ብር ብቻ
የፕሮግራሙ መጀመሪያ ሰዓት
9:00 ሰዓት ይሆናል።
ማሳሰቢያ
ያለን ክፍት ቦታ ውስን ስለሆነ እስከ ሰኞ ሐምሌ 5/2014 ዓ/ም ድረስ ክፍያውን በቶሎ በመፈጸም የዚህ ልዩ ቀን ተካፋይ በመሆን ዘመን የማይሽረውን ታሪክ
አብረን እንስራ እንላለን።
በድጋሜ እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ
የ2014 ዓ/ም የጂሲ ኮሚቴ