Get Mystery Box with random crypto!

ሶቅራጦስ በአቴና አደባባይ ሲዘዋወር ሳለ አንድ ጠቢብ ሰው ስለፅናት ሲያስተምር ያያል፡፡ ሶቅራጦስ | የፋኖስ ንፅረቶች (✍በአይሳነው)

ሶቅራጦስ በአቴና አደባባይ ሲዘዋወር ሳለ አንድ ጠቢብ ሰው ስለፅናት ሲያስተምር ያያል፡፡ ሶቅራጦስ የጠቢቡን ሰው ንግግር በማቋረጥ ጽናት ምን እንደሆነ ይጠይቀዋል፡፡ ሰውየውም ሲመልስ፡-
‹‹ፅናትማ ጠላት እየቀረበህ ቢመጣም ከቦታህ ሳትነቃነቅ መጠበቅ ነው›› አለው፡፡ ሶቅራጦስም፡-‹‹እቅድህ ከሽፎ መሸሽ ቢኖርብህስ?›› ሲል ይጠይቀዋል፡፡ ጠቢቡም፡-‹‹በርግጥ በዚያን ጊዜ ፅናት ሌላ ይሆናል፡፡›› ሲለው ሶቅራጠስም ‹‹ስለዚህ ፅናት ከቦታህ አለመነቃነቅ ወይም ከቦታህ አለመሸሽ ካልሆነ ታዲያ ፅናት ምንድነው?›› ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ጠቢቡም ሰው ለጥያቄው የሚሰጠው መልስ ተቸግሮ ‹‹አሁን ሳስበው በትክክል ጽናትን የማውቀው አልመሰለኝም፡፡›› አለው፡፡

ሶቅራጦስም፡- ‹‹እኔም አላውቀውም›› ‹‹ነገር ግን ፅናት አዕምሮህን መጠቀም ነው፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን እንኳን ትክክለኛውን ነገር ብቻ ማድረግ ከቻልክ ያ ፅናት ነው፡፡›› በማለት ተናገረ፡፡
*ብቻ ዝም መለት ባለብክ ግዜ ዝም መለት *መናገር ባለብክ ጊዜ መናገር
*መሮጥ ባለብክ ጊዜ መሮጥ
*መቃወም ባለብክ ጊዜ መቃወም
*መደገፍ ባለብክ ጊዜ መደገፍ
አዎ! ትክክለኛውን ነገር በትክክለኛው ጊዜና በትክክለኛው ቦታ ማድረግ መቻል ፅናትም፣ ብልሃትም ነው ሃሳብህ ሲራቀቅ፣ ዕውቀትህ ሲጠልቅ፤ ተግባርህ ሲፀድቅ ምንም ዓይነት የሕይወት ፈተና አይጥልህም ለዚህም ምስጥሩ ማንበብክ ነው ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ።
"ሰላም ለ ሓገራችን ሰላም ለ አለማችን ።

@fanwithay