Get Mystery Box with random crypto!

ታላቅ ደስታ አለን በሰማይ! ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! በቅርብ ጊዜ የሚወደን | INTIMACY TV (FLG Church)

ታላቅ ደስታ አለን በሰማይ!
ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች!
በቅርብ ጊዜ የሚወደን አዳኝ፣ የተባረከው ተስፋችን፣ ዘላለማዊ ክብራችን፣ ፅኑ ደስታችን እና የዘላለም ህይወታችን የሆነው የክብር ንጉሳችን መሲሁ ኢየሱስን ፊት ለፊት ልናየው ነው!

ቅዱሳን በርቱ ይህ አሁን የምንኖረው የምድር ዘመን አልቆ #አዲስ ምዕራፍ ሊጀመር ነው፤
“በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ።”
ራዕ21፥5
እነሆ በክርስቶስ የመጀመሪያው መምጣት ጊዜ የጀመረው አዲስ ነገር ሁሉ ሙሉ በሙሉ አዲስ ሊሆን ነው! ስለዚህ
"ከእኛ ማንም ለራሱ የሚኖር፣ ለራሱም የሚሞት የለምና። ብንኖር ለጌታ እንኖራለን፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን፤ ስለዚህ ብንኖርም ብንሞትም የጌታ ነን።" ሮሜ 14:7-8
ተብሎ እንደተፃፈ፣ ለራሳችን የምንኖርበትን ቅኝት አስተካክለን የህይወት ግባችንን ዘላለማዊው ላይ እናድርግ!
አሁን ንጥቀት እና ሞት አንድ የሚያደርጋቸው ፍፃሚያችን ወደሆነው ዘላለማዊ ቤታችን መውሰዳቸው ነው።
ተወዳጆች ሆይ ልባችሁን አበርቱና ከምድር የኑሮ ስበት፣ በክርስቶስ ሆነንም ባለን-በያዝነው-ባገኘነው አለመርካትን-በቃኝ አለማለትን አስወግዱ! የፈጣሪውን መልክ ለመምሰል በእውቀት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችኋልና በመንፈሳዊ እውቀት እደጉ።
በዚያ ታላቅ ደስታ እና ሁሉ በሙላት አዲስ በሚሆንበት የክብር ቀን ላይ እንገናኝ ዘንድ በርቱ!

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።”
(2ቆሮ 13፥14)

ከነብይ ዳዊት አለሙ
#የሕያው_እግዚአብሔር_ቤተሰብ_ቤተክርስቲያን
June 27-2022