Get Mystery Box with random crypto!

ይህንን ያውቁ ኖሯል አለማችን ላይ ከሚሰሩ ስራዎች ያልተለመዱ እና ግርምትን የሚጭሩ አስገራሚ የ | አስገራሚ እውነታዎች 🌍 - @fact_ethiopia

ይህንን ያውቁ ኖሯል

አለማችን ላይ ከሚሰሩ ስራዎች ያልተለመዱ እና ግርምትን የሚጭሩ አስገራሚ የስራ ዘርፎች ለዛሬ 3 ስራዎችን ልናስቃያችሁ ወደድን አብራችሁን ቆዩ....

1 - ጎበዝ እንቅልፋምይህ የስራ አይነት የሚሰራው በሀገረ ፊንላንድ ሲሆን!..የሰራተኞቹ ዋነኛ ስራ ሙሉ ቀን መተኛት ሲሆን የስራው ዋነኛ ዓላማ በፊንላንድ ለሚገኘው አንድ ሆቴል ውስጥ ለሚያስገቧቸው አዳዲስ አልጋዎች ሙሉ ቀን ተኝቶ ግምገማ መስጠት ነው፡፡(ስራው ለሴቶች ብቻ ነው!)

2 - የሙሉ ጊዜ ፊልም ተመልካች ይህ ስራ ደግሞ እንደ Netflix livestream ያሉ ፊልም ማሳያዎች ላይ ለእይታ ከመድረሳቸው በፊት (አስቂኝ ፣ አስፈሪ ፣ አስደሳች ነው ወይስ ደባሪ ነው የሚሉትን አስቀድሞ አስተያየት በመስጠት አሪፍ ደሞዝ ይከፈላቸዋል፡፡

3 - የእባብ መርዝ አላቢ ይህ ስራ ደግሞ እጅግ ድፍረትን እና ጀግነትን ይጠይቃል! ስራው አደገኛ ከሚባሉ የእባብ ዝርያዎች ውስጥ መርዛቸው ብቻ በማውጣት በአንድ ላይ ማከማቸት ሲሆን   አሰሪዎቹ የእባቡን መርዝ በመጠቀም ለተለያዩ በሽታዎች መድሀኒት መስሪያነት ይጠቀሙበታል፡፡

የቱ አስገረማችሁ? እናንተስ የትኛው ስራ ላይ መቀጠር ትችላላችሁ?Comment ላይ

3ተኛውን እኮ የሚል አይጠፋም

𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄

       @FACT_ETHIOPIA
       @FACT_ETHIOPIA