Get Mystery Box with random crypto!

1ኛ . ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ፈጣሪህን አመስግን ለሊቱን በዙሪያ ባደሩ መናፍስት በሞት ልትወ | የሬጌው👑 ንጉስ🇪🇹™

1ኛ . ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ፈጣሪህን አመስግን

ለሊቱን በዙሪያ ባደሩ መናፍስት በሞት ልትወሰድ ስለነበር

2ኛ ሙሉ አካል ስላለህ

አካልህ ሙሉ ባይሆን እንኳን በጤና አልያም በህይወት ያቆየህ ፈጣሪ ምክንያት ስላለው ነው ለዚህም አመስግነው

3ኛ ቢያንስ በቀን አንዴ እንኳን አፍህን ትሽራለህ ቢኖር መርጠህ በልተህ ባይኖርህ ውሀ እንኳን ጠጥተህ ትውላለህ ለዚህ የፍጥረታት ጌታን አመስግን

4 . በመንገድህ ሁሉ ስትሄድ ሠላምታ እና ትህትና ከአንደበትህ አይራቅ

5. ለሚገጥምህ መጥፎ ነገር ሁሉ ምላሽህ ደግ እና መልካም ነገር ይሁን
ክፉ ተነጋግረህ ክፉ ሰርተህ ከሰውም ከእንስሳውም ከሁሉ ፍጥረት ከምትጣላ ይልቅ ሁሉን እንዳመጣጡ በፍቅር ሸኘው

6. ባረፍክበት ሁሉ እርዳታህን ለሚሻ ሁሉ ደግ ልቦናህን እና ቀኝ እጅህን አትከልክል የዛሬ ቸርነትህ የነገ እረፍትህን ያበጃጃል እና

7. ከማንም ጋር በማይረባ ጊዜያዊ ጥቅም አትጣላ አትጋጭ ችኩል አትሁን ለሚያልፍ ቀን ብለህ ፍፁም አትማረር ይልቅ ይቅር ማለትን ቅድሚ መስጠትን ለልብህ አስተምር ላንተ ያለው እንጀራ ሳይሻግት ሳይደርቅ በለምለምነቱ በጊዜው ከነሌማቱ ቤትህ ይገባልና

8. ህፃናትን ሁሉ በአንድ ልብ ውደድ ሠው ማፍቀርን ሀቀኝነትን እና ደግነትን አስተምራቸው ነገ በድካምህ ጊዜ ሮጠው የሚደርሱልህ እነሱ ስለሆኑ
ወጣት እኩዮችህን አትናቅ አንተ የደረስክበት እንዲደርሱ እርዳቸው ከአንተ የበለጡም ስለሚኖሩ ራስህን ለማሻሻልም የሚረዳህ ቸር ማድረግ ነውና ከፍ ለማለት የሌሎችን ጫንቃ አትስበር እንዲያው እጅ ለእጅ ተያይዞ መለወጥን አስብ
አዛውንቶችን አተጨቁን ምርቃታቸው ርግማናቸውም ከአፋቸው ጠብ አይለምና ከፈጣሪ እንዳትጣላ

''የሚያድግ ህፃን አይጥላህ
የሚሞት ሽማግሌ አይርገምህ''

9. ስላለህም ስላጣኸውም ሁሉ አመስግን ስላሣለፍከው መከራም ስላየኸውም ተድላ በምክንያተ አመስግን የሚሆነው ሁሉ በምክንያት ባንተ ላይ ስለተከናወነ አመስግን ማማረር ከቶ ስለማይበጅ

10. ስላሣለፍከው ቀን ሁሉ ምሽት በቤትህ ለፈጠረህ አምላክ ምስጋናን አቅርብ ብዙዎች አንተ ያየኸውን ቀን ሳያዮ ብዙ እየተመኙ በህይወት ወደማይቀረው አለም አልፈዋልና

።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ክፉ እንድናስብ እንድንፈፅም ከዚያም በራሳችን እንድናዝን እንድንፀፀት የሚያረገን የክፋት አባት እሱ ሠይጣን ነውና እሱን በቸርነት በመልካም ስራና በየእምነታችን በፈጣሪ ምስጋና እንበቀለው እንጉዳው

ከዚህ በላይ ጉዳትና በቀል የለም
ሰው ሳይሆን ሠይጣን ነውና ጠላታችን
በሱ ላይ ነው በቀለኝነታችን




Sh Like are To Ur Frien
@eyobreggae
@eyobreggae
•═••• •••═•
~~~~~~~~~~~~~~