Get Mystery Box with random crypto!

ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበው ቡና 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ | Extol ™

ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበው ቡና 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

ሐምሌ 3/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ካቀረበችው የቡና ምርት 1ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የግብርና ሚኒስትሩ ዑመር ሁሴን ገለጹ።

ይህ ገቢ የተገኘው ወደ ውጭ ከተላከው 300 ሺሕ ቶን የቡና ምርት መሆኑን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በዚህ ዓመት የተገኘው ገቢ በዓመት በአማካይ ይገኝ ከነበረው ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ500 ሚሊየን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱንም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ይህ ግብ እንዲሳካ ላደረጉ የቡና አምራቾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!