Get Mystery Box with random crypto!

ከመፅሐፍ ገፅ 📙®

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewuketmad — ከመፅሐፍ ገፅ 📙®
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewuketmad — ከመፅሐፍ ገፅ 📙®
የሰርጥ አድራሻ: @ewuketmad
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 442
የሰርጥ መግለጫ

፦ በዚህ ቻናል የሚዳሰሱ ነገሮች
፦ የሀገራችን ታሪኮች
፦ እውነታዎች
፦ የ ሀገር እና ባህር ማዶ ፍልስፍናዎች
፦ የስነ ልቦና ምክሮች
፦ የአያቶቻችን ተረቶች (Bed time story )ይሉታል ነጮቹ
፦ ፖለቲካዊ አድምታ በእኔ እይታ
፦ PDF መፅሐፍት እና ግጥሞች
Group @ewuketmad2
አስታየት፡ ጥያቄ እና ጥቆማ
@Areg05
@Areg07 አድርሱን

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-01-01 11:10:34 አንድ ኪሎ ቅቤለዳቦ ጋጋሪ የሚሸጥ ገበሬ ነበር።አንድ ቀን ዳቦ ጋጋሪው ገበሬው የሚሸጥለት ቅቤ በትክክል አንድ ኪሎ አለመሆኑን ይደርስበታል። በሁኔታው በጣም ስለተበሳጨ ገበሬውን ለፍርድ ቤት ይከሰዋል። ዳኛው ገበሬውን ቅቤውን እንዴት እንደሚመዝን በጠየቁት ጊዜ "የተከበሩ ዳኛ እኔ ኋላ ቀር ገበሬ ነኝ ቤቴ ውስጥ ሚዛን እንጂ የሚዛን ድንጋይ የለኝም" በማለት መለሰ ። " እና ቅቤውን እንዴት ነው ምትመዝነው"በማለት ዳኛው ጠየቁት። በዝህ ጊዜ ገበሬው" የተከበሩ ዳኛ እሱ ቅቤ መግዛት ከመጀመሩ በፊት ከእሱ ላይ አንድ ኪሎ ዳቦ ገዛው ነበር። አናም ለእሱ ቅቤ መሸጥ ስጀምር በየቀኑ አንድ ኪሎ ዳቦ ይዛልኝ ስመጣል ዳቦውን ሚዛን ላይ በማስቀመጥ እኩል ክብደት ያለው ቅቤ መዝኜ እሸጥለታለው። ለዝህ ተጠያቂ መሆን ያለበት እኔ ሳልሆን ዳቦ ጋጋሪው ነው" በማለት መልስ ሰጠ



በህይውት ውስጥ የምናገኘው ለሌሎች የሰጠነውን ነው

አንድ ቀን በሰፈርነው ልክ መሰፈራችን አይቀርም ስለዝህ ከጥፋት እና ክፋት እንራቅ

ዛሬ ላይ ትንሽ መስሎን የምናጠፋው ጥፋት እስከ ህይውታችን ፍፃሜ አብሮን ይጓዛል

ደግነት፡ ለጋሽነት ፡ መዋደድን እንጂ ክፋትን፡ ንፉግነትን ፡ ጥላቻን ማለያችን አይሁት


Http://t.me/ewuketmad
67 viewszk, 08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 13:56:04 ስነምግባር ምንድነው ?
ስነ ምግባር ማለት በፅኑነት ማፍቀር መቻል ነው ።
ሥነምግባር አቅጣጫን ማሳየት መቻል ነው ።
ስነምግባር ችግር ከመፈጠሩ በፊት መከላከል መቻል ነው ።
ሥነምግባር እምቅ ሃይልን በተሻለ ምርጥ መንገድ ማዘጋጀት መቻል ነው
ሥነምግባር ለማንም የምንሰጠው ሳይሆን ለምናስብላቸው የምንሰጠው ውድ ስጦታ ነው ።
ስነምግባር ፍቅርን ይገልፃል ።


http://t.me/ewuketmad
96 viewszaki, 10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 22:55:40 ዮጋ


ዛሬ ስለ ዮጋ ትንሽ እናውጋችሁ
ዮጋ የምለው ቃል መሰረቱ የሳንስክሪት ቋንቋ ስሆን ትርጉሙም ውህደት ወይም ጥምረት ማለት ነው ። ጥምረቱም ሰውነት ፡ አእምሮ እና መንፈስ አንድ ላይ ተባብረው የሚደረግ ሲሆን ሶስቱም በስምምነት ስሰሩ፦ ጤና ፡ ሰላም እና ደስታ ማግኘት ቀላል ይሆናል ።

ዮጋ ከ5,000 ዓመት በፊት በህንዶች የተፈጠረ ሲሆን ብዙ ዘመናት በጥቂቶች እጅ ብቻ ቆየ በኃላ ከክርስቶስ መወለድ በኋላ በ200 ዓ.ም #ፓታንጃል የተባለ ግለሰብ የዮጋን ፍልስፍና ተግባራዊ ልምምድ ለመጀመሪያ ግዜ አሰባስቦ #ዮጋ -ሱትራስ በሚል ርዕሰ ፃፈው ። ይህ ሰው እስከ ዛሬ የዮጋ አባት በመባል ይታወቃል ። ከረጅም ግዜ በኃላ 1983 ዓ.ም ስዋሚ ቪቫንካንዳ የተባለ ግለሰብ በአሜሪካ አንድ ትልቅ ኮንፈረንስ ላይ አስተዋወቀ ።


Http://t.me/ewuketmad
105 viewszk, 19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 21:18:43 የዩንቨርሲቲ ተማሪ ከፕሮፈረሰሩ አስማሪው ጋርመናፈሻው ላይ
ቁጭ ብለው
ያወራሉ፡፡ አስተማሪውከተማሪዎችሁሉ ይህን ተማሪ በጣም ስለሚወደው እንደ
ጓደኛው
አድርጎነው ሚያየው፡፡ፊት ለፊታቸው ጫማውን አውልቆ የመናፈሻውን
ጵዶችናሳሮችን
የሚያስተካክል ሰራተኛ አለ፤ተማሪው የጵዳት ሰራተኛውንእያየለአስተማሪው
“ቲቸር ዛሬ
አንተም እኔም ደብሮናል፤ ለምንያኛውን ሰውዬ ትሪክ አንሰራውም? ያወለቀውን
ጫማ
ደበቅእናርግበትና ጫማዎቹን ሲያጣቸው እንዴት እንደሚበረግግእኛም
እዛጋደበቅ ብለን
እንመልከተው” ይለዋል፡፡አስተማሪውም“ወጣቱ ጓዴ ምንም እንኳ ቢደብረን
ድሃዎችን
እያሰቃየን እኛመደሰት የለብንም፡፡ ባይሆን እኛ ገንዘብ አለን በገንዘባችንየበለጠ
ደስታን
ማግኘት እንችላለን፤ ሂድና ቀስ ብለህ ሰውዬውሳያይህ ባወለቀው ጫማዎች
ላይ ገንዘብ
ከተህበት ና፤ ከዛምተደብቀንየሚሆነውን እናያለን” አለው፡፡ተማሪው
አስተማሪውእንዳለውቀስ
ብሎ የሰውዬው ጫማላይ በርካታ ገንዘብ ከቶበት መጣናከአስተማሪው ጋርደበቅ
ብለው
የሰውዬውን ሁኔታ መከታተልጀመሩ፡፡ሰውዬው ፅዳቱን ጨርሶ ኮቱን ለበሰና
ጫማውን
ለማድረግሲታገል ይቆረቁረውና ጎንበስ ብሎ ጫማውን ሲያራግፈውብሮችን
ያገኛል፡፡
ሰውዬው ደነገጠ!! ዙሪያውን ቢያይ ማንምየለም፤ ደግሞ ደጋግሞ ቀኝና ግራ
ሲመለከት
ማንም ሰውየለም፡፡ ሰውዬው በአግራሞት አንገቱን እየነቀነቀ ገንዘቡንኪሱ
ውስጥ ከከተተው
በሗላ ሁለተኛ እግሩጫማውን ለማድረግ ሲያነሳ በተመሳሳይ ገንዘብ
ያገኛል፤ሰውዬው
አላመነም!!በጉልበቱ ተንበረከከ አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀና አደርጎ ጮክብሎ
“ጌታዬ
የሚስቴን መታመም አውቀህ ነው አይደል፤ካንተ ሌላ ማንም እንደማይረዳት
አውቀህ ነው
አይደል!!የልጆቼ ዳቦማጣታቸውን አይተህ ነው አይደል!! ምስጋና ይግባህ ጌታዬ”
አለ፡፡
ተማሪው የሰውዬውን ሁኔታ ሲመለከትልቡን ነካው አይኑ እንቧ አቀረረች፡፡
አስተማሪውም
“ቅድም ካሰብከው ትሪክይልቅ አሁን የተሻለ ደስታ እንዳገኘህ አልጠራጠርም”
አለው፤ተማሪው እንባውን እየጠረገ “ፕሮፌሰር እስከዛሬ ካስተማሩኝሁሉእንደዚህ
ያለ
ትምህርት አስተምረውኝ አያውቁም፤ በህይወቴየማረሳውን ትምህርት ነው
ያስተማሩኝ፤
እውነትምከመቀበልመስጠት የተሻለ ነው” በማለት መለሰላቸው፡፡ "ደግ
ደጉንእናስብ
መልካምነት መልሶ ይከፍላልና



http://t.me/ewuketmad
155 viewszk, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 10:05:43 አንድ የደሃ ቤተሰብ ልጅ እጅግ በጣም የሃብታም የሰፈሩን ልጅ ያፈቅራል፣እንዲሁ
በ ሰፈር ጓደኝነት አብረው ጥሩ ጊዜ ካሳለፉ በኋላ በውስጡ የሚቀጣጠለውን
ፍቅሩን ለመግለጽ ቀን እና ሰአት ጠብቆ የፍቅር ጥያቄ ያቀርብላታል: እሷም
ይህን መለሰች "ምን አልክ?! ፍቅረኞች እንሁን?!፣ካንተጋር ጊዜ ማሳለፌን በሌላ
ተረድተኸው ከሆነ ተሳስተሃል፣በዛላይ እኔና አንተ ይምንመጣጠን ሰዎች
አይደለንም አንተ መናጢ ደሃ ነህ በወር የምታገኘውን ገንዘብ እኔ በአንድ ሰአት
ከጓደኞቼ ጋር ማጠፋት ናት በምን ልታኖረኝ ነው? ይሄን ሃሳብህን ተውና ሌላ
ምትመጥንህን ሴት ፈልግ እኔ እንደሆነ መቼም ላፈቅርህ አልችልም" ይሄን
ብላውም ልጁ በፍጹም ሊጠላት አልቻለም፣ ስለገፋችው ብቻ ከሷ ራቀ ልቡ ግን
ሁሌም እሷ ጋር ነበር ከ10 አመታት ቡሀላ አንድ ቀን እንዳጋጣሚ ሱፐር ማርኬት
ውስጥ ከልጅቷ ጋር ይገናኛሉ: "አነተ እንዴት ነህ? አለህ እንዴ? አሁንማ እዛ ጋር
መኪና ውስጥ እቃ የሚያስገባውን ምርጥ ሰው አገባሁኝ ስማርት ነው በዛ ላይ
በወር ስንት እንሚያገኝ ታውቃለህ 15,000 ብር ይሄን ሚበልጥ ደሞዝ ካለህ
አሁንም እድሉ አለህ ሃሃሃሃ..." ልጁ ከአስር አመት በኋም ይሄን ቃል
ከሚያፈቅራት ልጅ በድጋሚ መስማቱ አስለቀሰው፣ እንባዎቹን እየጠረገ ሳለ
የልጅቷ ባል መጣና:- "ጌታዬ ባለቤቴን ተዋወቃት" አለና ወደ ልጅቷ ዞሮ:
"ይገርምሻል ይሄንን ሱፐር ማርኬት እና ሌሎች በሚሊዮን የሚቆጠር ካፒታል
ያላቸው ድርጅቶች ባለቤት የሆነው አለቃዬ እሱ ነው: እስካሁን አላገባም: አንድ
በጣም የሚያፈቅራት ልጅ ነበረች በንጹህ ፍቅር የወደዳት ልቧን ግን ማሸነፍ
አላቻለም: እንዴት ያለ መልካም ሰው መሰለሽ: መቼም እሱን ያገኘች ሴት
በሁሉም ነገር አላህ ፈጣሪ የባረካት እድለኛ ሴት መሆን አለባት።


http://t.me/ewuketmad
167 viewszk, 07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 10:18:41 ሰናይ ቀዳሚት


አንድ ትንሽዬ አይጥ ነበረች እናም ሁልጊዜ ድመት በአየች ቁጥር ፈጣሪን " ፈጣሪ ሆይ ድመት አድርገኝ" እያለች ትፀልይ ነበር። እናም ፈጣርም ድመት አደረጋት። አሁንም ግን ውሾችና ከሷ በላይ የሆኑትን በአየች ቁጥር መፍራቷ አላቆመም። አሁንም እንዲህ ስትል ለመነች "አባክህ አምላኬ ሰው አድርገኝ" አለች። ፈጣሪም ልመነዋን ሰምቶ ሰው አደረጋት። ግን አሁንም የዱር አራዊት ስታይ መፍራቷ አላቆመም። አሁን እንዲህ ብላ ፀለየች " እባክህ የእንሰሶች ሁሉ አላቃ የሆነውን አንበሳ አድርገኝ" ፈጣሪም አንበሳ አደረጋት። ግን አሁንም ከአዳኞች መሸሿ አቆመም። በመጨረሻም ወደ ማንነቴ መልሰኝ ብላ ለመነች።



ማንም ሰው ከማንነቱ ውጭ መኖር አይችልም
ምናልባት እንደሆነ ሰው መሆን እንፈልግ ይሆናል ግን መሆን አንችልም እኛ እኛ ነን የራሳችን የተሰጠን ውብ ማንነት አለን

ሁላችንም ያጠለቅነውን የውሸት ጭምብል እናውልቅ

. http://t.me/ewuketmad
223 viewszk, edited  07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 23:32:32 ድሮ ጊዜ አንድ በባህር ዳሪቻ የሚኖር አላዋቂ ነበር ሁሌም ስፀልይ አትማረኝ እያለ ነበር ። አንድ ቀን እንደዚህ እያለ ስፀልይ የሰሙት ፓፓሶች እንደሱ አይደለም ማረኝ እያልክ ፀልይ ብለውት በመርከብ ባህሩን አቋርጠው ጉዞቸውን ቀጠሉ። እነሱ ራቅ እንዳሉ ያሉት ጠፍቶበት በባህሩ ላይ እየሮጠ ደርሶባቸው ምን ብዬ ልፀልይ አላቸው። እነርሱም በባህር ላይ እየሮጠ መምጣቱ ገርሟቸው በለመድከው ፀልይ ብለውት ጉዟቸውን ቀጠሉ።

አንዳንዴ የራሳችንን ትተን የሌሎችን እንመኛለን ። ምንም ስተት ብሆን እንደ ራሳችን ነገር የምሆን የለም










ሃሳባቹውን @ewuketmad2







ያካፍሉን የዚህ ፔጅ አባል ስለሆኑ እናመሰግናለን
ከወደዱት share ማድረግ እንዳይረሱ

http://t.me/ewuketmad
206 viewszk, 20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 22:30:19 አንድ የህግ ባለሙያ በባቡር እየተጓዘ ሳለ አንድ
በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ መጥታ ፊት ለፊቱ ከሚገኘው ወንበር ላይ
ተቀመጠች። በዚህም የህግ ባለሙያው ደስ አለው። ቀና ብሎ ሲመለከታት አይን
ለአይን ተያዩ ከዛም ፈገግ አለች። አሁን ደግሞ በይበልጥ ደስ አለው። ትንሽ
ቆይታ አጠገቡ ሄዳ ተቀመጠች። በዚህን ጊዜ እጅግ በጣም ደስ አለው። ትንሽ
ቆየችና ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ በሹክሹክታ "ያለህን ገንዘብ; የATM ካርድህን
ከነፓስ ዎርዱ እና የሞባይል ቀፎህን አሁኑኑ ካልሰጠኸኝ ስትጎነትለኝ እንደ
ነበረና ፆታዊ ትንኮሳ እንደደረሰብኝ እዚህ ባቡር ውስጥ ላሉት ሁሉ በመንገር
እጮኃለሁ።" አለችው። የህግ ባለሙያው በቸልተኝነት ቀና ብሎ ተመለከታትና
ከቦርሳው ውስጥ ወረቀትና እስክሪብቶ አውጥቶ እንዲህ ብሎ ፃፈላት "ይቅርታ
መናገርና መስማት የተሳነኝ ነኝ። እባክሽን ማለት የፈለግሽውን ሁሉ እዚህ
ወረቀት ላይ ፃፊልኝ።"
ልጅቷም ቀደም ብላ ስትነግረው የነበረውን ሁሉ ጽፋ ሰጠችው።
የህግ ባለሙያው ወረቀቱን ተቀብሏት በጥሩ ሁኔታ አጥፎ ኪሱ ከከተተው በኋላ
ከተቀመጠበት ተነስቶ ጎርነን ባለ ድምጽ ምን ቢላት ጥሩ ነው "አሁን
እንደፈለግሽ መጮህ ትቺያለሽ።"
የታሪኩ ምግባር: ሰነድን በአግባቡ መያዝ ምን ግዜም አስፈላጊ ነው።





http://t.me/ewuketmad
249 viewszk, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 10:57:01 እባብ በህይውት እያለ ጉንዳን ይመገባል
እሱ ሲሞት ጉንዳኖች ይመገቡታል።


አንተ ጠንካራ ልትሆን ትችላለህ። ግን አንድነገር አወቅ የቀን እንጂ የሰው ጀግና የለም።




አንድ ዘፍ አንድ ሺ የክብሪት እንጨት ልወጣው ይችላል ግን በአንድ ክብሪት እንጨት ሁሉንም ማጥፋት እንችላለን።


እንቅስቃስያችን በመልካምነት እና ቅንነት ይሁን

የዘራነውን ነው እና የምናጭደው፡ በየአንዳንዱ እርምጃችን በጥንቃቄ ይሁን።

ዛሬ በግድየለሽነት የፈፀምነው ተግባር ነገ ይደርስብናልና።






ሰናይ ሰንበት


ሀሳብ @ewuketmad2




http://t.me/ewuketmad
247 viewszk, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 23:52:39 #መሪ_ከመሆኔ_በፊት_ሰው_ነበርኩ

በማለት የተባበሩት አረብ ኤምሬትን መስርተው ለወግ ማዕረግ ያበቋት ሼኽ ዘይድ ተናግረው ነበር። አልፎ አልፎ መኪናቸውን ራሳቸው እየነዱ ወደ አንድ ድርጅት/ መሥሪያ ቤት ይሄዱና የሰውን ችግር ይመለከቱ ነበር።

ይህን ተግባር የተመለከቱ አንድ የጎረቤት መሪ "እርስዎ ንጉስ ሆነው እንዴት የተራ ሰው ስራ ይሰራሉ " ብለው ቢጠይቃቸው። "# ነጉሥ_ ከመሆኔ_ በፊት'ኮ ሰው_ነበርኩ " በማለት እንደ መለሱለት አማካሪያቸው የፃፈው ታሪክ ይገልፃል።



የኛ ሐገር መሪዎችስ መሪ ከመሆናቸው በፊት ሰው አልነበሩም ወይስ "ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል " የሚለውን ተረት እየተገበሩ ይሆን ?


ትናንት ስለዘርኝነት አስከፊነት ያወሩ ሰዎች ዛሬ ዘረኛ ሆነው ማየት ምንኛ ያሳፍራል


ችግሩ የት ጋርስ ይሆን ከወንበሩ ወይስ ከሰዎቹ።

ለመሪዎቻችን አንድ ነገር ማለት ፈልጋለው መሪ መሆን ከልቻላቹ ሰው ለመሆን ሞክሩ ምክንያቱም ሰው_መሆን ይቀድማል




http://t.me/ewuketmad
255 viewszk, 20:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ