Get Mystery Box with random crypto!

ያለውና የነበረው የሚመጣው አንዲት በአረብ ሀገር የእስልምና እምነት ተከታይ የነበረች ሴት ወደ አ | "ልጆቼ የቤተክርስቲያንን ነገር አደራ"

ያለውና የነበረው የሚመጣው

አንዲት በአረብ ሀገር የእስልምና እምነት ተከታይ የነበረች ሴት ወደ አንድ የግብፅ ካህን ጋር በመሄድ አባቴ አጥምቁኝ አለቻቸው።

ካህኑም አንቺ የእስልምና እምነት ተከታይ ነሽ
እናም አስቀድመሽ ልትማሪ ልታምኚ ይገባል አሏት
እርሷም እኔ ክርስቲያን ነኝ ሁሉን ነገር ራሱ ክርስቶስ አስተምሮኛል አንድታጠምቁኝ እፈልጋለሁ አለቻቸው።

ካህኑም በመገረም ለመሆኑ በማን ስም ነው የምትጠመቂው አሏት?

በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማናቸው?

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ልዩ ሦስትነት ያላቸው አንድ አምላክ ነው።
"አብ አምላክ ነው። ወልድ አምላክ ነው። መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው። ግን ሦስት አምላክ አይባልም አንድ ልዩ አምላክ ነው። አለች

"ይህን እንዴት አወቅሽ?

በራዕይ ዩሐንስ ላይ፦
“ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።” ራእይ 1፥8

ይህ ስለ ጊዜ የተነገረ ነው፦

ትላንትም ጊዜ ነው። ዛሬም ጊዜ ነው። ነገም ጊዜ ነው። ነገር ግን ትላንት ዛሬ አይደለም። ዛሬም ትላንት ወይንም ነገ አይደለም። ነገም ትላንት ወይንም ዛሬ አይደለም። ሦስቱም ግን ጊዜ ናቸው። ነገር ግን በአንድ ላይ የተጨፈለቁ አይደሉም። ትላንት ለብቻ ነው፣ ዛሬ ለብቻው ነው።፣ነገም ለብቻው ነው።

እንዲሁም፦

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው።
ነገር ግን አብ፥ ወልድ አይደለም፣ መንፈስ ቅዱስም አብ አይደለም። ሦስቱም በህልውና አንድ አምላክ ሆነው ይኖራሉ እንጂ።

እንዲህ አድርጎ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮኛል አለቻቸው።

ካህኑም እጅግ በመደነቅ ከልብ ለሚፈልጉት ለልበ ንፁሐን ምሥጢርን የሚገለጥ ክርስቶስን እያደነቁ አጠመቋት።