Get Mystery Box with random crypto!

ኃጢአቷን የምትጽፈዉ ሴት አንዲት ሴት ነበረች ኃጢአቷን የምትጽፍ ልቧ በኃጢአት የሰከረ ለኃጢአትም | "ልጆቼ የቤተክርስቲያንን ነገር አደራ"

ኃጢአቷን የምትጽፈዉ ሴት
አንዲት ሴት ነበረች ኃጢአቷን የምትጽፍ
ልቧ በኃጢአት የሰከረ ለኃጢአትም ተገዥ የሆነች ይች ሴት የተለያየ ኃጢያት የምትሰራ ናት ትዘሙታለች፣ ትዋሻለች፣ ታማለች፣ ተሰርቃለች፣ ትገድላለች፣ በአል ትሽራለች፣ በትእቢት የተሞላች ሴት ናት ልቧ ኃጢአት ነበር። ነገር ግን የምትሰራዉን ኃጢአቷን ሁሉ እየጻፈች ታስቀምጥ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን የጻፈችዉን ኃጢአቷን ብታየዉ ስንክሳር አክሎ ተመለከተችዉ ስንክሳር ማለት በ365 ቀኖች የሚለዉ የቅዱሳን ታሪክ ሰብስቦ የያዘ ትልቅ መጽሐፍ ነዉ። የዚች ሴትም ኃጢአትም ይህን አክሎ ነበር እንዳየችዉ ደነገጠችና ኃጢአቷን ተሸክማ አባት ወደ አለበት ወደ አንጾኪያ ሄደች አባ ባስልዮስን አገኘችዉ አባቴ በዚህ ያለዉ ኃጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችዉ።
አባ ባስልዮስም ይፋቅልሽ አላት ገልጣ ብታሳየዉ ሁሉ ተፍቆ አንዲት ኃጢአት ብቻ ቀርታ አየቻት። በጣም ከባድ ኃጢአት ነበረች ሊፈሩዋት የምትከብድ ሊነግሯት የምታሳፍር ነበረች አባቴ ይችሳ አለችዉ አባ ባስልዮስም ይችን ኃጢአትሽንስ ማስተሰረይ የሚችል ልጄ ቅዱስ ኤፍሬም ነዉ ሂደሽ ለእርሱ ንገሪዉ አላት።
አባ ባስልዮስ ይሄን ያላት ኃጢአቷን መፋቅ አቅቶት አይደለም የራሱ ክብር ከሚገልጥ የቅዱስ ኤፍሬም ክብር እንዲገለጥ ፈልጎ ነዉ። ደግሞም ስትመላለስ ንስሐ እንዲሆናት ጭምር ነዉ።
እሷም አባ ባሰስልዮስ እንዳላት ቅዱስ ኤፍሬም ወዳለበት ወደ ሶሪያ ሄደች በባዶ እግሯ እንቅፋቱ እየመታት እሾሁ እየወጋት እግሯ ሲደማ ልብሷን ቀዳ እየጠመጠመች ተጉዛ ከቅዱስ ኤፍርም ደረሰች።
አባቴ በዚህ ያለዉ ኃጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችዉ ቅዱስ ኤፍሬም ግን ይሄ ለኔ አይቻለኝም ለአባቴ ለአባ ባስለዮስ እንጂ አላት ቅዱስ ኤፍሬም ግን ኃጢአቷን መደምሰስ አቅቶት አይደለም በፈሊጥ ቀኖና ሲሰጣት እንጂ ስትመላለስ ኃጢአቷ እንዲቀልላትም ነዉ። ሂደሽ ለአባ ባስለዮስ ንገሪዉ ይደመስስልሻል አላት እሷም አግኝቸዉ እኮ አይሆንልኝም ብሎ ወደ አንተ ልኮኛል ሳትል እሽ ብላ መንገድ ስትጀምር እንደ ቀድሞዉ በህይወት አታገኝዉም ሙቶ ካህናት ሊቀብሩት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዘዉት ሲሄዱ ታገኝዋለሽ ሳትጠራሪ የተጻፈዉ ኃጢአትሽን ከአስክሬኑ ላይ ጣይዉ አላት እሷም እሽ ብላ ሄደች የቀኑ ሙቀት የሌሊቱ ብርድ እያሰቃያት ደረሰች ሙቶ ካህናት ፍትሀት እየፈቱት አየች።
የእግዚአብሔር አገልጋይ ባስልዮስ ሆይ የባሪያህን ኃጢአት ደምስስልኝ ብላ ከአስክሬኑ ላይ ጣለችዉ አስክሬኑም ድምጽ ወጥቶ ኃጢአትሽ ተደምስሶልሻል አላት ገልጣ ብታይ ተደምስሶላታል። አምላኳን አመሰገነች በደስታ ዘመረች በዚህ በኋላ ዓለምን ንቃ ገዳም ገብታ መኖር ጀመረች።
እንደዚች ሴት ኃጢአቱን የሚያስታዉስ ማነዉ?
ወደ ካህን ሂዶ ንስሐ የገባስ ስንቱ ነዉ?
ስለ ኃጢአቱ በረሃ የተከራተተ ማን ይሆን?
የዚችን ሴት መጨረሻ ያሳመረ የሁላችንም መጨረሻ ያሳምርልን ኃጢአቷን የደመሠሠ የሁላችንም ኃጢአት ይደምስስልን!
ለንስሐ የሚሆን ፍሬ አድርጉ
የዉዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ @Ewnetgen