Get Mystery Box with random crypto!

«መጅሊስ» የኢትዮጵያ ሙስሊሞች [መሻኢኸ-ሱፊያ] ያቋቋሙት ታሪካዊ ተቋም? ወይስ የ አንጃ ሽብራዊ | እውቀት ብርሃን

«መጅሊስ» የኢትዮጵያ ሙስሊሞች [መሻኢኸ-ሱፊያ] ያቋቋሙት ታሪካዊ ተቋም? ወይስ የ<ወሃቢዝም> አንጃ ሽብራዊ አስተምህሮ መፈልፈያ?!


በታላቁ ዓሊም <ሸይኽ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ> እና በባልደረቦቻቸው ህይወትን መስእዋት በመክፈል የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋም «መጅሊስ» ባለቤቶቹ የጥንት የጠዋቱን እስልምና የሚከተሉት «አህሉ-ሱና ወል ጀማዐ/ ሱፊያ» መሆናቸው ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው።
-
“ደፋር እና ጭስ...” እንዲሉ በመንግስት ጣልቃ ገብነት ይህን የ«አህሉ-ሱና» ተቋም ለሽብር አስተምህሮ አንጋቢው <ወሃቢዝም> አሳልፎ መስጠትም አስነዋሪ እና ህዝበ-ሙስሊሙ ይቅር ሊላው የማይችለው፣ የገዢውን ታሪክ ጥላሸት የቀባ፣ ህግና ሥርዓትን የጣሰ አሳፋሪና ነውረኛ ውሳኔ መሆኑ ጊዜ አብሮ ያሳየናል።


በመንግስት ጣልቃ ገብነት «አህሉ-ሱና»ውን መፈንቅለ-መጅሊስ ያደረገበት፣ በነ <ኢብራሂም ቱፋ> የሚመራው የ«ወሃቢዝም» አንጃ ማን ነው?

በአለም አቀፍ ደረጃ የዛሬ 300 አመት ገደማ፣ እንደ ሃገራችን ደሞ 30 አመታትን ያስቆጠረው የቂሎች ስብስብን ያከማቸው የ«ወሃቢዝም» አንጃ ታሪኩ «ጥቁር» ብቻ እና ብቻ ነው። የእስልምና ልሂቃን መጽሃፎችን አንብቡ! «ወሃቢዝም» የገባበት ሃገር ሲወድም እንጂ ሲለማ በታሪክ ታይቶ አይታወቅም። ሊቢያ፣ ዒራቅ፣ ሶሪያ፣ ጀዛኢር፣ የመን፣ አፍጋኒስታንና ሌሎች ሃገራት እንደ አብነት የሚጠቀሱ ናቸው።
-
«ወሃቢዝም» በእስልምና ስም የመጣ የወጣቶችን አዕምሮ መራዥ እና ደም አፋሳሽ ቡድን እንጂ ከእስልምና ጋር የሚያገናኘው መርህ የለም። ምክንያቱም የአይሁድ ስለላ ድረጅት ሰለባ የሆነው መሪያቸው <ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ> ይህን መመሪያ አስቀምጦላቸዋል። መመሪያውም እንዲህ የሚል ነው፦


«من دخل في دعوتنا فله ما لنا وعليه ما علينا، ومن لم يدخل معنا فهو كافر حلال الدم والمال»
ትርጉም፦ <<(ወሃቢ ሁኑ ወደ ሚለው) ጥሪያችን የገባ እኛ የምናገኘውን ያገኛል፤ በኛ ላይ የሚመጣውም በርሱ ላይ ይመጣል። እኛ ጋር ያልሆነ ግን ይህ ሰው ካሃዲ ነው፤ ደሙን ማፍሰስ (መግደል) እና ገንዘቡን መውሰድ ይፈቀዳል።>>


ይህን ጥሪ መሰረት በማድረግም ይህ አንጃ ከተመሰረተበት እለት አንስቶ እነርሱን ያልተከተለ በሙሉ በ«ከሃዲነት» በመፈረጅ የሙስሊሞችን ህይወት ሳይቀር ቀረጣጥፏል። የቡድኑ አደራጃጀት ጅማሮም ከሽፍቶች እና በስርቆት ራሳቸውን ካደራጁ የማፊያ ቡድን ስብስብ ሲሆን.. በነዚህ በመመካትም <ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ> ባስተጋባው የ ጂሃድ ጥሪ በሳኡድ አረቢያ ገጠራማ አካባቢ ሲኖሩ የነበሩ እረኞች ንብረትና ህይወት ወድሟል።

የ«ወሃቢዝም» ድርጅት በሳኡድ አረቢያ እና በኳታር የገንዘብ ድጎማ እሹሩሩ ተብሎ ያንሰራራ ሲሆን፣ አስተሳሰቡን በገንዘብ አማካኝነት ረጭቶ ሃገራችን መድረሱም አሳሳቢ ጉዳይ ሁኗል። በተለይ በመንግስት አማካኝነት «መፈንቅለ-መጅሊስ» ያደረገው አካል ይህን አስተምህሮ የሚረጭ መሆኑ ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል።
-
በሃገራችን ባሉ የ«ወሃቢያ» ት/ቤቶች የሚሰጠውን መጽሀፍ ያየ የልጆጃችንን አዕምሮ እና ርህራሄ ከእንጭጭነታቸው የሚነጥቅ መርዛማ አስተምህሮ መሆኑን ያረጋግጣል። የሚፈልግ ሰውም አይቶ እውነታውን ማወቅ ይችላል። ታዲያ ሃገራችን ወዴት እየሄደች ነው? «አህሉ-ሱናውስ» የዚህን አስተምህሮ አካሄድ እንዴት ሊቀበለው ይችላል? ፈፅሞ አይቀበለውም። ህገ-ወጡ መጅሊስም አይመራውም።


ተቋሙን በግዳጅ የተነጠቀው «አህሉ-ሱና ወል ጀመዐ/ ሱፊያ» ማን ነው?

«አህሉ-ሱና/ ሱፊያ» ከ1400 አመት በላይ ያስቆጠረውን፣ በ«አስሐመተ ነጃሺይ» ፍትህ አማካኝነት ወደ ሃገራችን የገባውን፣ ከትውልድ ትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ.. በጠነከረ ሰንሰለት ቅብብሎሽ እኛ ጋር የደረሰውን የጥንት የጠዋቱን የእስልምና አስተምህሮ የሚከተል ትክክለኛው የሙስሊሙ ክፍል ሲሆን።
-
ይህ ሰላም-ወዳዱ ማህበረሰብም እስልምናውን ከምንም በፊት አስቀድሞ፣ በእምነቱ ሳይደራደር እና ዓቂዳውን ሳይሸጥ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙት እንዳለው የሚመሰከርለት፣ ግቡ እምነት እንጂ ሽብር ያልሆነው አካል ነው። የእስላሙ ቀደምት ታሪኩም ይሁን መመለሻው ይኸው በደጋጎች የተዋበው መዳረሻ ብቻ ነው።
-
ይህ የደጋጋጎች መናገሻም አሁን አሁን በመሰረተው ተቋም ባይተዋር ተደርጎ በመንግስት ጣልቃ ገብነት ቷቋሙ ለ«ወሃቢያ» መሰጠቱ ከባድ ጥያቄን ያስነሳል። የቀጣዩ ትውልድ ዕጣ-ፈንታም ያሰጋል። በዝምታ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም።
-
በነገራችን ላይ «እስልምና» እና «ወሃቢዝም» ፈጽሞ አይገናኙም። ወሃቢያ በእስልምና ስም የመጣ የአይሁድ ተልዕኮን ያነገበ የሽብር ቡድን እንጂ ከእስልምና ድርሻ የለውም። እርሱንም በዝርዝር እንመለስበታለን። ለዚህም አሁን ያለው #ህገ-ወጥ መጅሊስ ሙስሊሙን አይወክለውም።