Get Mystery Box with random crypto!

የተሸከርካሪ ምርት ዘመንን መረጃ ለማግኘት የሚረዱ አሰራሮችን ስለማሳወቅ ስለ ተሽከርካሪ መረጃ አስ | ኤቫን መንጃ ፈቃድ ማሠልጠኛ ተቋም

የተሸከርካሪ ምርት ዘመንን መረጃ ለማግኘት የሚረዱ አሰራሮችን ስለማሳወቅ
ስለ ተሽከርካሪ መረጃ አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል የምርት ዘመን አንዱ ነው፡፡ በምርት ዘመን ላይ የሚፈጠር ልዩነት የለም፡፡ ምክንያቱም የምርት ዘመኑ ዲክለራሲዮን ላይ በግልፅ የሚቀመጥ ነው፡፡
ይሁንና ቀድሞ የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች በወቅቱ የምርት ዘመን ካልነበራቸው የተሽከርካሪ አገልግሎት አሰጣጥና ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር 19/2010 አንቀፅ 22የምርት ዘመን የሌላቸው ተሽከርካሪ ምዝገባ በሚለው ስር ምዝገባ የሚከናወንበትን አግባብ በግልፅ አስቀምጧል፡፡
1.ማንኛውም ተሽከርካሪ የሻንሲ ቁጥር ያለው ሲሆን ካለው የሻንሲ 17 ቁጥር ዲጂት በሻናሲ ቁጥር የስሪት ዘመን በመውሰድ የምርት ዘመን ተወስኖ ወይም
2.ከአስመጪዎች የስሪት ዘመን መረጃ ከመረጃ ቋት(ሲስተማቸው) መውሰድ ወይም
3.የተመሳሳይ ተሽከርከሪ ሞዴል ፈልጎ የምርት ዘመን መወሰድ ወይም
4.Commercial invoice የተገዛበት የተቆረጠበት ዘመን እንደ ምርት ዘመን መውሰድ ወይም
5.ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ተሽከርካሪዎቹ አዲስ ከነበሩ የገቡበትን ዘመን እንደ ምርት ዘመን በመውሰድ ወይም
6.ያገለገሉ ተሽከርካሪዎቹ ከነበሩ ከመግባታቸው በፊት የነበራቸው እድሜ እና ሀገር ውስጥ ከገቡ ቦኃላ ያገለገሉበትን ዘመን ደምሮ ያገለገሉበት ዘመን በመውሰድ ወይም
7.ሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ ከሆነ የተገጣጠሙበትን ዘመን እንደ ምርት ዘመን በመውሰድ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን
8.ከኢንተር ኔት ላይ Vin በማስገባት ከኢንተርኔት በማውረድ የሻንሲ ቁጥሩን በመፃፍ የምርት ዘመን መለየት የሚቻል መሆኑን በዚህ መልክ የማይገኝ ከሆነ ግን ተሽከርካሪው በተመዘገበበት ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መረጃውን ማግኘት የሚቻል መሆኑ እንገልፃለን::
መረጃ:- የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን