Get Mystery Box with random crypto!

ቀን፡ 13/06/2015 ዓ.ም የምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ | Eupheus Ethiopia

ቀን፡ 13/06/2015 ዓ.ም
የምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ በ2015 ዓ.ም ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
ጉዳዩ፡ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ የካቲት 20/2015 ዓ.ም ብቻ መሆኑን ስለማሳወቅ
በቅድሚያ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን ምርጫችሁ አድርጋችሁ እኛ ጋር ለመማር በመፍቀዳችሁ ታላቅ ኩራት ይሰማናል፡፡ አያይዘንም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን የካቲት 20/2015 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በእለቱ በተመደባችሁበት ህንጻ እንድትገኙ እናሳስባለን።
ዝርዝር አጠቃላይ የምዝገባ እና የገለፃ መርኃ ግብርን የተመለከቱ መረጃዎችን እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው በኩል የሚተላለፉ ሌሎች መረጃዎችን የዩኒቨርሰቲው መገናኛ ዘዴዎችን በመወዳጀት፣ በማጋራትና የደውል ምልክቷን በመጫን ወቅታዊ መረጃዎችን መከታተል ትችላላችሁ፡፡
University Official Website: www.aastu.edu.et
University Official Facebook Account: https://www.facebook.com/aastu.edu.et
University Official You tube Channel: https://www.youtube.com/channel/UCUpgXuqDCiLfgLPK_FxS-6g

ዝርዝር የምዝገባና የገለፃ መርሃ-ግብር እንዲሁም ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ቅድመ-ሁኔታዎችን ከላይ በተመለከተው ሰንጠረዥ ውስጥ መመልከት ይቻላል፡፡
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሬጂስትራር ጽ/ቤት