Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የ ASTU ተማሪ Channel ቤተሰቦች እንደመን ከረማችሁ (እእእሺ  ጌጤ | Eupheus Ethiopia

ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የ ASTU ተማሪ Channel ቤተሰቦች እንደመን ከረማችሁ (እእእሺ  ጌጤ መጣሽ ደሞ )። አዲሱን Semesterራችሁነ የጀመራችሁ መልካም ትምህርት፤ Final ልትፈተኑ ያላችሁም መልካም ፈተና እያልኩ አንድ የምስራች ላብስራቹ።

-የምስራች

-ምሥር ብላ ምን ተገኘ

-አልጫ ከሆነ ይመቸኛል

-ቀልደህ ሞተሃል ምኑ ነው ሲያስጠላ

-ምን መሰለሽ...

-አልፈልግም ተወው በቃ

-ተወው በቃአአአ... ወላቃ!

-ውልቃት ይዘዝብህና ተናገር ምትናገር ከሆነ

-ምን መሰለሽ... ASTU ተማሪ ስሙአን ልትቀይር ነው።

- ውይ ውይ ደህና ስም ያላት ይመስል

- ዋ! እንዳላፈራርስሽ

- ውይ ፈራሁ በጣም ... እሺ ቶሎ ቶሎ ንገረኝ አሁን ስራ አለብኝ እኔ

-እንደውም አንቺ አታስፈልጊም ተዪው ለ Memberሮቿ ነግራቸዋለሁ

ውድ የ ASTU ተማሪ Channel ቤተሰቦች ይህ የምስራች ድምፅ ነው። ASTU ተማሪ ተደራሽነቷን ከ አንድ ግቢ ውሱንነት ወደ ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ Channelነት ለማሳደግ በማሰብ ስሟን ልትቀይር ወስናለች። የስሟ መቀየር ምክነያት ተደረራሽነቷን ለማስፋት ብቻ ሳይሆን ለተከታዮቿ የምታቀርበውንም Content ጨምሮ ሙሉ በሙሉ በአዲስ ስርዓተ-ትምህርት (መለቴ ስርአተ   ...post) ለተከታዮቿ መቅረብ ስላሰበች ነው።

#አዲሱ_ስም
ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት በአዲስ ስርዓተ-ልጠፋ (ስርአተ-post ሳይሻል አይቀርም ) ነው ASTU ተማሪ ልትቀርብላችሁ የወሰነችው። አዲሱ ስርአተ-post ከሚለውጣቸው ነገሮች አንዱ Channelሉ ላይ  ትምህርት ነክ የሆኑ ጉዳዮችን በቁም ነገር እያዋዛ (ሙሉ ቀልድ ስለሆነ ) ለአንባቢዎቹ ለመድረስ መሞከር ነው። ለዛም ነው #ASTU_ተማሪን ወደ #EUPHEUS_ETHIOPIA ለመቀየር የተወሰነው። EUPHEUS (ኢውፊየስ) የ ግሪክ ቃል ሲሆን እውቀትን ፍለጋ የሚል የአማርኛ አቻ እና Active seeking of knowledge የሚል ደግሞ የኢንግሊዘኛ ፍች ይኖረዋል። ከዚህ በኋላ እስከተወሰኑ ጊዜያት ድረስ ደግሞ ለ አዲስ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ተማሪዎች መረጃን በመስጠት ግንባር ቀደም የመረጃ ምንጭ የሆነ የዩኒቨርሲቲ ቻናል ለመሆን ቃል ይገባል። (ትገባለች...ከየት ጀምሮ ነው ፆታዋን የቀየርኩት )

Eupheusን ይዞ ወደ እወቀት ጉዞ



╔═.✵.══════════╗
   ꧁ @EUPHEUS_ETHIOPIA ꧂
╚══════════.✵.═╝