Get Mystery Box with random crypto!

(....ስላንቺ....) (ቢኒያም ወጋየሁ) . . እቴ....ፈቅደሽ እኔን ክፉ አልምደሽ እቴ. | ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ

(....ስላንቺ....)
(ቢኒያም ወጋየሁ)
.
.
እቴ....ፈቅደሽ
እኔን ክፉ አልምደሽ
እቴ....ወደሽ
እኔን ልቤን ክደሽ
ከኔ.....
ጠፋው አንቺ ሄደሽ
... ታዲያ ለኔ...
ከመፋቀር ለተጣጣው
... ታዲያ ለኔ...
በመገፋት ለተቀጣው
... ለህይወቴ...
ይህ ነው ዕጣው?
ታዲያ ላንቺ...
በደስታ ጥግ ለተከበብሽ
ታዲያ ላንቺ...
በማጠውለግ ዙር ለከበብሽ
በፅናትሽ አንቺ ላበብሽ
ፍቀጂልኝ ልሁን ልብሽ።
ከዛማ
ወደ ጻማ
ወደ ፍጥረት:ፍቅር አበው:ሕልውና
ለአርዮስ:የተቃርኖ:ቅድስና
አሳረፈኝ:ከጥጉ ላይ:ይህ ጎዳና
ለምዶሽ አንቺን:በርኖስ ሆነኝ:የእግርሽ ዳና
እንደ ሀገር.....እንደ ማገር
እንደ እውነት...እንደ ክህነት
የሌለሽ ቃል:የስማዚያ:ብኩንነት
ስም ያሳጣሽ:የራሙኤል:ስም ጭፍራነት
አንቺ....
የዘመኔ:ረቂቅ እውነት
ሆነሽ ሳለ
ቀን ያሳያል:መሄድሽን:እየሳለ

የመሄድሽ:ሽንቁር ችንካር:ተቸክሎ
የመምጣትሽ:ግማ እውነት:ተከልክሎ
እንዴት ልየው:ስሜታችን:ዳስ አክሎ
መልመድ"መግመድ":ሆኖ ቢኖር:ባልተከፋው
በልኬቴ:በተሰፋሽ:በልኬትሽ:በተሰፋው
ለአንደበቴ:ይህ ነው ተስፋው
ስትርቂ ግን
ከመኖሬ ተሰረዝኩኝ:እኔ ከኔ ባንቺ ጠፋው።
እቴ...
እኔን ክፋ አልምደሽ
እኔን ልቤን ክደሽ
ጠፋው አንቺ ሄደሽ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
@yotorr