Get Mystery Box with random crypto!

#ነዳጅ የመስከረም ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል። የንግድ እና ቀጣ | EBS TV

#ነዳጅ

የመስከረም ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል።

ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረገው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል።

ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በመስከረም ወር 2015 ዓ.ም እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia