#ATTENTION
ሰቆጣ !
የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በማስመልከት ውሳኔዎችን አሳልፏል።
- ማንኛውም እግረኛ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።
- ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጣቸው ተሸከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ተሸከርካሪ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
- ከጸጥታ መዋቅሩ ውጭ በየትኛውም ሰዓትና ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
- ማህበረሰቡን የሚያውኩ የሃሰት አሉባልታዎች / የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት ተከልክሏል።
- ተፈናቃዮች ከተሰጣቸው የመጠለያ ካምፕ ውጭ መንቀሳቀስ በብቅ ተከልክሏል።
- ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ባንክ ቤቶች፣ ሱቆች፣ ሆቴል እና መስል የመንግስትና የግል ድርጅቶችን መዝጋት በጥብቅ ተከልክሏል።
- በከተማው የሚገኙ የመንግስትና የግል ታጣቂዎች መንግስት በሚያሰማራው የፀጥታ ስራ ላይ ተሳታፊ የመሆን ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
- ማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ግለሰብ ሆነ ድርጅት የትኛውንም ሚዲያ ተጠቅሞ የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት፣ በተለይ ስለጦርነቱ አሉቧልታ መዘገብ ሆነ መግለጫ መስጠት በጥብቅ ተከልክሏል።
- ማንኛውም የቤት አከራይ ወይም አልጋ ቤቶች ተከራዮቻቸውን የመለየትና የገለሰቦቹን ማንነት የሚለይ ህጋዊ መታወቂያ ስለመያዛቸው የማረጋገጥ ግደታ አለባቸው።
- ማንኛውም የከተማው ማህበረሰብ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር የመቀናጀትና የመተባበር ግዴታ አለበት።
እንዚህ በማይከብር ላይ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ታዟል።
@tikvahethiopia