Get Mystery Box with random crypto!

#በእውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ_ለይ_የተመሰረተ ተስፋ ያጣች ሴት | Fun ethiopia😂🤣

#በእውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ_ለይ_የተመሰረተ

ተስፋ ያጣች ሴት

ክፍል

...ኪሩቤል አጠያይቆ ሀና መኖሯን እርግጠኛ የነበረ ቢሆንም ቴድሮስ ግን በውሸት አሳምኖ እንደሌለች ነግሮታል... ኪሩቤልም በማርፈዱ እያዘነ የሃናን እንጀራ አባት ተሰናብቶ ሄደ... ከሰአታት ቡሃላ ሀና ተመለሰች ለመውለድ አንድ ወር ቢቀራትም ሀና ግን ደስተኛ አይደለችም ልጇን ገና ሳትወልደው ማክቤል ብላ ትጠራዋለች ማክቤል ማለትም (በማልፈልገው ቦታ የወለድኩት የምወደው ልጄ) ማለት ነው። ሀና ቀኗ ደርሷል እናቷም በደስታ ልጇን ለማረስ የገንፎ እና የአጥሚት እህል ቅቤ ቡላ... የቀራት የለም ሁሉን አዘጋጅታለች ሀናም ኮንዶምንየም ቤቷን አከራይታ ጥሩ ገንዘብ ታገኛለች ፀጉር ቤቷንም ቀጥራ ታሰራበታለች ስለዚህ በገንዘብ ደረጃ ቤተሰብ አታስቸግርም... ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ሀሙስ ቀን የሀና ታናሽ ወንድም ወረቀት ይዞ መቶ ለሀና ሰጣት ሀናም በፍጥነት ገልጣ ማንበብ ጀመረች ኪሩቤል ነው... "ሀኒ የእንጀራ አባትሽ ቴድሮስ እንድንገናኝ ስላልፈለገ እንደሌለሽና ድጋሚ' ሀና አለች?' ብዬ እንዳልመጣ አስጠንቅቆኛል ታናሽ ወንድምሽ ነው መኖርሽን የነገረኝ ሀኒዬ እኔ እንድርቅሽ ብለሽ ነው አይደል (ኤች አይ ቪ) አለብኝ ብለሽ የዋሸሽኝ? ግን ተመረመርኩ ውሸትሽን እንደሆነ አረጋገጥኩ ያን ቀን ስሜታዊ ሆኜ ጥዬሽ በመሄዴ ግን አፈርኩ እናም ይሄን ሁሉ ግዜ በፍቅርሽ ስደሰት በመለያየታችን ስከፋና ሳዝን ቆየሁ ሀኒ አሁን ግን አንድ የሚያረገንና ይቅር የሚያባብለን ልጅ በሆድሽ ይዘሻል እናም የኔ ውድ ይቅር በይኝና ሽማግሌ ልኬ ልውሰድሽ እንጋባና አዲስ ህይወት እንኑር ፍቀጂልኝና ደስተኛ ላርግሽ... ያንቺው ኪሩ" ይላል... ሀና አንብባ እስክትጨርስ እንባዋ ወረቀቱን ያጥበው ነበር "ሁሌም ኪሩ ያለጥፋቱ ይቅርታ ይጠይቃል!" አለች ለመንሳት እየጣረች አንብባ ጨርሳ ወንድሟን ጠርታ ኪሩቤል ጋር እንዲወስዳት ስትጠይቀው ድንገት ቴድሮስ መጣ ይሄኔ "የት ልትሄጂ ነው?" አለ ሀናም የውስጥ ንዴቷ እየተፈታተናት አንተ በውሸት የለችም ብለህ ያባረርከው የልጄ አባት ጋር አለች ቴድሮስም ዲቃላሽን አርፈሽ ውለጂና አሳድጊ እንዲ ሆድሽ ተንገፍጥጦም ወንድ ትመኛለሽ? አላት ፈገግ እንደማለት እያለ... ሀና ንዴቷን መቆጣጠር አቃታት "ስማኝ ቴድሮስ አንተ ማለት ልጅነቴን የነጠከኝ ክፉ ሰው ነህ እናቴ የበደልከኝን በደሎች ብታውቅ ዝም የምትልህ ይመስልሃል ግን ምን አይነት ክፋ ነህ እስቲ ዛሬንኳ አንደበትህን አርመው የህፃን ገላ ለወሲብ ጥማትህ የተጠቀምክ አሳፋሪኮ ነህ..." አለች ሀና ከንዴቷ ብዛት የምትናገረውን መምረጥም ማን ካጠገቧ እንደነበር ማስተዋልም አልቻለችም ነበር ... ግን ይሄ ዋጋ አስከፈላት እናቷ የሁለቱን ምልልስ ስሰማ ስለነበር ደምግፊቷ ጨምሮ እራሷን ሳተች የእናቷን መውደቅ ያየችው ልጅም እናቷን ለማዳን አምቡላንስ ጠራች ሆኖም የሀና እናት የልጇን ልጅ ሳታይ ልጇንም ሳትጠግባት እስከወዲያኛው አሸለበች... የእናቷን ሞት መቋቋም ያልቻለችው ሀናም እናቷ ቀብር ላይ እንኳ ለመገኘት ሳትታደል ቀረች በድንጋጤ በመውደቋም ያለቀኗ ለመውለድ ተገደደች........


#ክፍል ይቀጥላል..... ለጓደኞቻችሁም አጋሮአቸው

ፍቅር እና ሳቅ
⚘➣ @etsubawi ❥
══•ೋ•✧ ೋ✧•══
ሼር SHARE