Get Mystery Box with random crypto!

'ህፃናት መች ነው ጥርስ ማብቀል ያለባቸው?' - ዶ/ር መሐመድ በሽር ፤ የህፃናት ሐኪም ህፃናት | Ethio pharmaceuticals and Health

"ህፃናት መች ነው ጥርስ ማብቀል ያለባቸው?" - ዶ/ር መሐመድ በሽር ፤ የህፃናት ሐኪም

ህፃናት እስከ መች መብቀል አለበት? ካልበቀለ መች ወደ ባለሙያ መመሄድ አለባቸው? የጥርስ መብቀል ከተቅማጥ በሽታ ጋር ይገናኝ ይሆን? ስለ ህፃናት የጥርስ እድገት ትንሽ ጀባ ልበላችሁ

ብዙ እናቶች ልጆቻቸው ጥርስ መች ማብቀል እንደሚጀምሩ በግልፅ ስለማያውቁ ልጄ እስካሁን ጥርስ አላበቀለም/ አላበቀለችም ብለው ጤና ተቋም ሲመጡ ማየት የተለመደ ነገር ነው። አንዳንድ እናቶች ደግሞ እስከመች ድረስ ሊያድግ እንደሚችል አያውቁም በዚህ የተነሳ እራሳቸውን ሲያጨናንቁ እናያለን ይህን ጭንቀታቸውን ለመቅረፍ እኔም ካነበብኩት ትንሽ ጀባ አልኳችሁ።

የህፃናት የጥርስ እድገት በጨቅላዎች እና በልጆችዎ ድድ ውስጥ የጥርስ መብቀልን ያመለክታል ይህ የሚጀምረው ብዙውን ጊዜ ልጅዎ ከ6 እስከ 8 ወር ዕድሜ ሲኖረው ሲሆን፡፡ ልጅዎ የ30 ወራት ዕድሜ ላይ ሲደርስ ሁሉም 20 የህጻናት ጥርሶች ቦታቸውን ይይዛሉ ፡፡

አንዳንድ ልጆች ግን ከ8 ወር ዕድሜያቸው በሗላም ቢሆንም ምንም አይነት ጥርስ ላያሳዩ ይችላሉ ፣ ይህ ግን ብዙውን ጊዜ የተለመደ ቢሆንም ምንም ጥርስ አስከ 13 ወር ካልበቀለ ለባለሙያ ማሳየት ይገባል፡፡

ብዙውን ጊዜ ሁለቱ የታችኛው የፊት ጥርሶች (የታችኛው ኢንሲዘሮች) ቀድመው ይበቅላሉ፡፡ ቀጥለው ሁለቱ የላይኛው የፊት ጥርሶች (የላይኛው ኢንሲዘሮች) ያድጋሉ፡፡

ከዚያም ሌሎች ወተት ጥርሶች (ኢንሲዘሮች) ፣ የላይኛውና የታችኛው መንጋጋዎች ፣ የውሻ ክራንቻዎች፣ በመጨረሻም የላይኛውና የታችኛው በጥልቀት የሚገኙት መንጋጋዎች ይበቅላሉ፡፡

ልከጆች ጥርስ ማብቀል ሲጀምሩ ምን አይነት ምልክቶች ያሳያሉ ??

- መነጫነጭ ወይም ብስጩነት ማሳየት
- ጠንካራ ነገሮችን መንከስ ወይም ማኘክ
- ልጋግ ማዝረብረብ ብዙውን ጊዜ ጥርስ ማደግ ከመጀመሩ በፊት የሚከሰት ነው
- የድድ ማበጥና መጠንከር
- ምግብ እምቢ ማለት
- የእንቅልፍ ለመተኛት መቸገር

መፍትሄውስ ምን ይሆን?

በዚህ ጊዜ ማድረግ ያለብን ልጅዎ የማያኝካቸው ቀዝቃዛ ነገሮች መስጠት። ለልጅዎ ለስለስ ያሉ ምግብ ይስጦቸው ፤ በቀስታ ጥርስ የሚበቅልበት ቦታ በእጅ መንካት። በዚህ መንገድ የልጅዎን የጥርስ እድገት አብረው በመሆን የተሳካ ያድርጉላቸው።