Get Mystery Box with random crypto!

የአሸባሪው ህወሃት ታጣቂዎች መጠለያ ጣቢያ በመግባት 25 ሰዎች በግፍ መገደላቸው ተነገረ። ታጣቂዎቹ | Mereja Daily

የአሸባሪው ህወሃት ታጣቂዎች መጠለያ ጣቢያ በመግባት 25 ሰዎች በግፍ መገደላቸው ተነገረ።
ታጣቂዎቹ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ወለህ የመጠለያ ጣብያ ገብተው በንጹሀን ዜጎች ላይ ግፍ አድርሰዋል።

"በቦታው ተገኝቼ ገንዤ ቀብሬያቸዋለሁ" ያሉት ተፈናቃይ ቄስ መስፍን አለሙ "አሸባሪ ቡድኑ በመጠለያ ጣቢያው ገብቶ ያላደረገው ግፍ የለም፤ ፍጹም እንዳንነሳ አድርጎ ነው የሄደው" ብለዋል።

ከ25ቱ ውስጥ ህጻናትና ሴቶች የበዙ ቢሆንም አዛውንቶችን ጭምር በጥይት ደብድበው መግደላቸውን ነው ቄስ መስፍን አለሙ የተናገሩት።

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበርያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰሎሞን ንጉስ እንደገለጹት፣ አሸባሪው ቡድን በመጠለያ ውውስጥ በመግባት ንጹሀንን በግፍ ጨፍጭፏል።

"ለሰው ነፍስ የማይራራው የህውሃት አረመኔ ቡድን ከዚህ ቀደም ከ90ሺ በላይ ተፈናቃይ ከቤት ንብረቱ እንዲፈናቀል አደረገ፣ ዛሬምም ይህን እኩይ ተግባር አዝሎ መጥቶ መጠለያ ካፕ ገብቶ በሰውና በንብረት ላይ ውድመት አድርሷል።" ብለዋል

አቶ ሰሎሞን በመጠለያው ውስጥ አንዲት እናት ከአራት ልጆቿ ጋር በግፍ ገድሎባታል ብለዋል።

ሀላፊው አያይዘውም በእርዳታ የተሰጣቸውን የዕለት ጉርሳቸውንም ጭምር ዘርፈው፣ ድንኳኑን ቀዳደውና ተፈናቃዮች የሚጋግሩበትን ማድ ቤት አፍርሰው፣ ምጣድ ሰብረው እንዳይነሱ አድርገዋቸው እንደሄዱ ነው የገለጹት።
በመጠለያ ጣብያው ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጉብኝት አድርገዋል።
====================
ፈጣን መረጃ ለማግኘት
@EtMerejaDaily
@EtMerejaDaily
በውሸት አካውንት እንዳትሸወዱ