Get Mystery Box with random crypto!

በሰቆጣ ግንባር  ወቅታዊ መረጃ 1ኛ. የግንባር መረጃ ።።።።።።።።።።።።።። የሰቆጣ ወረዳ | Mereja Daily

በሰቆጣ ግንባር  ወቅታዊ መረጃ
1ኛ. የግንባር መረጃ
።።።።።።።።።።።።።።
የሰቆጣ ወረዳ ቀበሌዎች ለአብነት  ወለህ፣ቲያ ፣ሐሙሲት ፣ብርብር ፣ ዋል፣ ዳብል ፣ እክመ ጽርዋ የሚባሉ ቀበሌዎች በጥምር ጦሩ ነጻ ሁነዋል።
መገናኛ  እና ፈንጅ ይዘው የተገኙ ሰርጎ ገቦች ተይዘዋል።
ከ802 በላይ የጠላት ሀይል እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
ከ50 በላይ የህወሃት ሀይል እጅ መስጠታቸው።
  በጥራሪ ወንዝ ወደ ገርፍ እየዘለሉ እየገቡ  በጎርፍ መወሰዳቸው፣
በሀሙሲት የነበረው የጠላት ጦር ወደ ኮረም እጅ አውጭኝ እያለ መፈርጠጡ 
ከጋዝጊብላ ወረዳ ዛሮታ ከህወሃት ነፃ መሆኑ፣
ከሰቆጣ ከተማ አስተዳደር 04 ቀበሌ ጽበያ እና ሚላካን  ጎጦች   ከጠላት ነጻ መሆናቸው፣
በዝቋላ ወረዳ ጥምር ጦራችን ቅዳሚት ድል እያስመዘገበ መሆኑ፣
2ኛ.የህወሓት ታጣቂዎች በያዙባቸው ቦታዎች ያደረሱት በደል በጥቂቱ ( የክፋት ጥግ )
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
  የአርሶ አደር ፍየል እየገደሉ መሔድ የአንድ አርሶ አደር  10  ፍየል  ተገድሏል።
ጤና ጣቢያዎችን መዝረፍ
ትምህርት ቤቶችን መዝረፍ
የንጹሀን ንብረት መዝረፍ
ንጹሀን ዜጎችን መግደል
አስገድዶ ገበሬዎችን  ከሀሙሲት እስከ በጻታ መስመር እስከ ጥራሪ ሬሳ ማሸከም ፣
ጥራሪ ወንዝ ተገደው የተወሰዱ ዜጎችን ወደ ጎርፍ ወርውሮ መጣል ከደረሱ በደሎች ጥቂቶቹ ናቸው።

3ኛ የሚስተካከሉ ጉዳዮች
።።።።።።።።።።።።።።
የዞኑ፣የሰቆጣ ወረዳ እና የሰቆጣ  ከተማ አስ/ ር የፖለቲካ አመራሮች በየቀኑ የሽሽት ገፈት ቀማሽ መሆናቸው (ሁሉምን አይመለከትም) ።

ጳጉሜ 2/2014 ዓ.ም
====================
ፈጣን መረጃ ለማግኘት
@EtMerejaDaily
@EtMerejaDaily
በውሸት አካውንት እንዳትሸወዱ