Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ ፊት አለ...! አንዳንድ ፊት አለ፣ ጸዳል ያበጃጀው ጮሌነት ያጀበው ማስመሰል የካነው በ | የሰላም መልዕክተኞች በኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹

አንዳንድ ፊት አለ...!

አንዳንድ ፊት አለ፣
ጸዳል ያበጃጀው
ጮሌነት ያጀበው
ማስመሰል የካነው
በህይወት ጅራፍ ውስጥ፣ ፈገግታ ማይከዳው
ሀዘን የማይደፍረው
ግና ከናቱ ሆድ እግዜሩ ሲቀርጸው
"ክፉም ደግ ቢገጥምህ ስቀህ እለፍ" ያለው!

ይብላኝ ለኔ ቢጤ ፣ለተቋጠረ ፊት
መላ ለማይፈታው ፣የእድሜ ዘመን መክሊት

ፍቅር ሳይነጥፍበት ሰውነት ሳይከዳው
የገጹ ቋጠሮ ከይሲ ላስመሰለው

ታደሰ ደምሴ

@Ethiovolunters