Get Mystery Box with random crypto!

ሁሌም በትክክል አስበህ ተራመድ። አስበህ ተናገር። ብትቆም እንኳ በትክክለኛው መንገድ ቁም። ሳታስብ | የሰላም መልዕክተኞች በኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ሁሌም በትክክል አስበህ ተራመድ። አስበህ ተናገር። ብትቆም እንኳ በትክክለኛው መንገድ ቁም። ሳታስብ አትናገር። ለሰው ስሜት ተጠንቀቅ። ስሜቱን የማይቆጣጠር ሰው አትሁን።

ሠራሁለት ለማለትና ሌላውን ለማናደድ አትትጋ። እንዲያ ከሆንክ የሰይጣን መ/ቤት ሆንክ ማለት ነው።

በትክክል በተናገርከው፣ በወሰንከው፣ በሠራኸው ጉዳይ ከፋኝ የሚል ካለ አትጨነቅ። ሁሉም አዋቂ ሰው በፈለገው መንገድ እንዲሄድ ሃራ ልቀቀው። ሃሳብህ ልክ ከሆነ የሄደ ሰው ሁሉ ወደፈለገበት በርሮ ዞሮ ተሽከርክሮ ፀሓይ በምእራብ ጠልቃ በድጋሚ በምስራቅ እንደምትወጣው ነገ ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም። ከመጣም መልካም፣ ካልመጣም ስህተቱ ካንተ አይደለምና ከስሁት ሰው ተገላገልክ!

ሁሌም አንተ በትክክል ለማሰብ ጣር፣ ተጣጣር እንጂ ሌላውን ሰው ወዳንተ ሃሳብ ለማምጣት አትታገል። ሰው ሃሳብን የሚቀበለው አዲስ ነገር ለመቀበል ባለው ዝግጁነት ልክ ነው። እንኳን ሃሳብና መድሃኒትና ህክምና እንኳ ለመሥራት የሚቀበለውን ይፈልጋል።

ቆንጆና ምርጥ ሃሳብ ከሌላው ሰው ካገኘህ ግን ለመቀበልም ለማድነቅም አታመንታ። ድንቅ ሃሳብ ስታገኝ በአንድ ሰዓት ውስጥ ለተግባራዊ እርምጃ እንቅስቃሴ ጀምር እንጂ አትቁም። ሃሳብ በተግባር ካልታጀበ እንደ ንፋስ ብን ብሎ ጠፊ ነው።
የሰው ማንነት የሃሳቡ ውጤት ነውና ሃሳብን ለማነጽ ትጋ!

ካነበብኩት ላይ