2022-06-14 10:09:24
(Maggie)
"እንደናንተ ዘመን ተሻጋሪ ...ባለ ብዙ ፍሬ ...ከንፁህ ልብ የተቀዳ ... በማስመሰል በውድድር እና በይሉኝታ ያልተፈተለ ..... ገንዘብ ውበት ዝና ና ክብር ሚባሉ ኮተቶችን ያልደረተ.... ድንገት ብልጭ ብሎ ደግሞ ድርግም የማይል....... የደረቀ ነፍስን የሚያለመልም.. አመድማ ገፅን የሚያወዛ.... ከእውነተኛ ማንነት የተጨለፈ መዋደድ.... መገኛው ወዴት ነው?" ብዬ ጠየቅኳቸው.. .....ገጠር ሄጄ የነበረ ግዜ.. ....... ከአያቴ የመጨረሻ ልጅ ከእታፈሱ ጋር ምንጭ ውሀ ልንቀዳ የሄድን ግዜ እንደሳቸው እድሜ ጠገብ ዛፍ ስር ቁጭ ብለው ያገኘዋቸውን የቀዬው ነዋሪ አዛውንትን
...
....
የህይወት ትልቁ ክፍል ላይ ተስፋ ቆርጫለው... ፍቅር ላይ!
.. ፍቅር ሸቀጥ ከሆነብኝ ከራረመ... በወንድ ኪስ ውስጥ እና በሴት ልጅ ውበት ስር የቀብር ስነስርዐቱን የፈፀመ ርካሽ ሸቀጥ!....(በተለይ በዚ ዘመን)
ዝግመተለውጡን የጀመረው ከራስ ነው!.... በነፈላስፎቹ ዘመን ፍቅር በጭንቅላት ይለካ ነበር.
ለጥቆ ወደ ልብ ወረደ! እራሱ ፍቅር(ክርስቶስ) መጥቶ ፍቅርን አነገሰው. ሰልሶ... ወደብልት ወረደ! የኛ ዘመን ላይ!.....የፍቅር ቀን በሚል የገበያ ስምኮ ሚደረገውን ብናገር ለቀባሪው ማርዳት ነው ሚሆንብኝ... እስቲ ተውት!......
አራትኛ ወደጉልበት አምርቷል... ይኸው ለጉድ የጎለተኝ መድሀኒያለም ክብሩ ይስፋና.... የኔ አልሆነችምና ፊቷ መበላሸት አለበት ብሎ አሲድ ሲደፋባት አይቻለው.....
:::::;;;;;;;:::::::::::::
ወደቀድሞው ልመለስማ
ሽማግሌው ....እድሜን ስክነትን ጥበብን ትዕግስትን እና ጥልቅ ማስተዋልን... መሬት ላይ ወድቆ አቧራን ቃም እንዳደረገ እርጥብ ልብስ ቅመውት....ፍፁም በተረጋጋ መንፍስ እንዲህ አሉኝ
.
.
"ልጄ.... ባሁኑ ዘመን ሁሉም ሰው ፍቅርን አድናቂ ብቻ ስለሆነ ነው! ዳር ቆሞ ብቻ ማድነቅ! የሰው ድግስ ላይ ከዳር እንደቆመ የበይ ተመልካች በምኞትና በህልም አለም እንደሚደሰት... መናኛ ሰው!.... ፍቅርኮ እጃችን ላይ ነው!
የተሳካላቸው ሰዎችን ስታይ ምነው እነሱን ባደረገኝ! ምነው ፈጣሪዬ መልካሙን ልክ የነሱ ያለውን የሞቀ ፍቅር በሰጠኸኝ.....ታድለው.. ትላለህ እንጅ... "እኔም አንድ ቀን..." ብለህ እጅህ ላይ ያለውን ፍቅር ለመዘርዘር አታልምም!
...... ታካች ትውልድ! .... እንኳን ሰውን ውሻን ለማልመድ መስዋዕት ትከፍላለህኮ! .... ምስያህን ለማልመድ ግን እንደው እንሰናከላለን.
በዛላይ.... እናንት ያሁን ዘመን ልጆች... በሳይንሱ በቀለሙ በጥበቡ... በሁሉም ላይ እንደተሳለ ሰይፍ ናቹ.... ግን... ፍቅር ላይ ይቀራዋል! ምድር ራሱ የቆመችው ፍቅር ሚባል መቋሚያ ተደግፋ ነው.
..... ፍቅርን "ባለቤት መሆን" ወይ በላባቹ እንዳደረጃቹት ቤት ንብረት"የእኔ ብቻ ሀብት! የኔ ንብረት" በሚል ስም ሸብልላቹ ያፈቀራቹት ወገን ድንገት ተቅፋቹ ገሸሽ ያለ እንደሆነ በፍቅር ላይ ተስፋ ትቆርጣላቹ!..... "ተከዳው!" "አወይ ሰው ማመኔ" ትላላቹ.....
ቀድሞ ነገር የጀመራቹት መች ፍቅር ሆነና?! ....ግብይት ይ?"
የጥጥ ማሳ የመሰለ ራሳቸውን ዳበስ አድርገው.... ቀጠሉ
"ወፊቱን በወጥመድህ ይዘህ ቤትህ ጎጆ ሰርተህ ጥሬ ወሀ እና መሰል ነገሮችን እየሰጠህ በድሎት ብታሳድጋትም እሷ ግን ከዛ ጎጆ መውጣትህ ሁሌ ትናፍቃለች
.. በተመሳሳይ... ይችኑ ወፍ ለቀህ እሯሷው የሯሷን ጎጆ ሰርታ ብትኖር ግን እጎጆዋ ለመመለስ እጅጉን ትናፍቃለች.... አየህ...
የሙጥኝ ብለህ ፍቅርን ስትይዝ እንደባህር ዳር ድንጊያ ያሟልጭሀል.... ነፃነቱን ስተሰጠው ግን... ቅንጭብ እንዳዋደደው ወረኧት የሙጥኝ ይልብሀል"
ሰው እጅግ የተወሳሰበ ፍጥረት ነው... መልአካዊ አመልና እንስሳዊ አመል አለው......... በመልአካዊው ያፈቅርበታል በእንስሳዊው ይበቀልበታል.........
ለዛኮ ነው ወንጌል ስሙ ቁርዐን ቅሩ መጣፍቅዱስ አንብቡ የሚባል.....
የምትወድዳት ሴት ውስጥ ያለውን እንስሳ ለመግደል መጀመርያ አንተውስጥ ያለውን አውሬ መግደል አለብህ!
ያኔ ማንንም የሚያ ስ ቀና እጡብ ድንቅ ፍቅር ትመሰርታለህ..."
ቀጭን ኩታቸውን ወደ ትከሻቸው እያጣፉና ሱፍ እንደተዘራበት ጥቁር መሬት በነጭ ጢም የተወረረ ፊታቸውን ዳስሰው
"እየውልህ.... ልጄ.... ... ክርስቶስ ፍቅሩን የገለጠው ቆስሎ ነው... አንተም ቁሰል ድማ አካልህን እጣ ወይ ደግሞ እንዲያ እንደክርስቶስ ያለውን አይነት ስ ቃይ ተሰቃይ አይደለም ያልኩት.... ትግስትን ገንዘብ አድርግ..... ማስተዋልን አስከትል.... ፍቅር ስሜት ብቻ አንዴ ቦግ አንዴ እል ም እንደሚል ተራ የሚሆነው.... ለሰጠኸው ፍቅር ምላሽ ስተጠብቅ ግዜ ነው. አፍቅር.... አንተውስጥ ያለው ፍቅር አገር ያህላል.... ትጎዳለህ እሱ እርግጥ ነው... ግን ጉዳትስ ቀን ጠብቆ ይክስሀል..... ፍስሀን በሰውነትህ ኮለል ያደርግልሀል...... ብቻ ታገስ .... "ቦ ጊዜ ለኩሉ!" አይደል ያለው ጠቢቡ!......... ስጥ ስጥ ስጥ..... ተስጠኸው አጥፎ ደርቦ የሰጥሀል.....ታድያ የሚሰትበትን ግዜ አታስላ.... እሱው በፈቀደው ቀን ይስጥህ."
ተመስጬ ነበር.....ካሉት ውስጥ አንድ ሀሰት የለበትም.
አንድ ነገር ተረዳው......... ግብዞች እንደሆንን... ወድደን ለካ በዛ ፋንታ መወደድን እንጠብቃለን??......
እታፈሱ እንስራውን ሞልታ ጨርሳ እንዳሻክማት ጠራችኝ...... ሽማግሌውን እጅ ነስቼ ሄድኩ
Magi
423 views07:09