Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioseberzina — ሰበር ዜና ETHIOPIA
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioseberzina — ሰበር ዜና ETHIOPIA
የሰርጥ አድራሻ: @ethioseberzina
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 181
የሰርጥ መግለጫ

አላማችን መረጃን በአግባቡ በጥራት በፍጥነት ማድረስ ነው፡፡ @Ethioseberzina

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-09 19:45:52
ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን አልምቶ ለመጠቀም ስምምነቷን ከሶማሊላንድ ጋር ዳግም ማጽናቷ ተሰምቷል!

ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የነበረውን በበርበራ ወደብ አልምቶ የመጠቀም መብቷ እንደማይነካባት በሶማሊላንድ ፕሬዚደንት በኩል ይፋ ሆኗል ሲል የምሥራብ የሬድዮ መጽሔት አስነብቧል፡፡

ከትናንት በስቲያ ወደ ሶማሊላንድ ከተማ ሐርጌሳ የኢትዮጵያ ልዑክ ማቅናቱንና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሁም በአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን ከሶማሊላንድ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ጋር መነጋገሩን የሶማሊላንድ ብሔራዊ ጣቢያ ተናግሯል፡፡

ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለማልማት ከሶማሊላንድና ከዲፒ ወርልድ ኩባንያ ጋር የጋራ ስምምነት እንደነበራት ይታወቃል፡፡ በዚህ ስምምነት 19 በመቶ የወደቡና ድርሻ የምትይዝ ሲሆን ባለፈው ወር ክፍያ ባለማጠናቀቋ ድርሻዋ ተነጥቋል ሲሉ የሶማሊላንድ የገንዘብ ሚኒስቴር መናገራቸውም ይታወሳል፡፡

ይህን የተናገሩት ሚኒስትር ጭምር በተገኙበት ፕሬዚደንታዊ የእራት ግብዣ የተደረገለት የኢትዮጵያ ልዑክ ስምምነቱ ባለበት አንደሚቀጥል ማስተማመኛ ተሰጥቶታል፡፡

(ኤሊያስ-መሰረት)
bbc_amharic1
36 viewsedited  16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ