Get Mystery Box with random crypto!

' እንወጣም ' - ተቃዋሚዎች የስሪላንካ ጉዳይ ዓለምን ማነጋገሩ ቀጥሏል። የስሪላንካ ፕሬዜዳንት | ሰበር ዜና ETHIOPIA

" እንወጣም " - ተቃዋሚዎች

የስሪላንካ ጉዳይ ዓለምን ማነጋገሩ ቀጥሏል።

የስሪላንካ ፕሬዜዳንት ከስልጣን ወርዳለሁ ቢሉም ተቃዋሚዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ለቀን አንወጣም ብለዋል።

የስሪላንካ ፕሬዜዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ መኖሪያ ቤትን የተቆጣጠሩት ተቃዋሚዎች ዛሬም ፕሬዝዳንታዊ መኖሪያውን እንደማይለቁ ገልፀዋል።

ተቃዋሚዎቹ የፕሬዜዳንቱን መኖሪያን ከተቆጣጠሩ በኃላና ፕሬዝዳንቱ በባህር ኃይል ታግዘው ከሸሹ በኃላ ከስልጣን እወርዳለሁ ቢሉም ተቃዋሚዎች ግን እስካሁን አልተቀበሉትም።

የተማሪዎች ንቅናቄ መሪ የሆነው ላሂሩ ዋራሴካራ ለጋዜጣኞች በሰጠው መግለጫ " ትግላችን ግና አላበቃም እሱ እስካልተወገደ ድረስ ትግላችንን እናቆምም " ሲል ተደምጧል።

ተቃዋሚዎቹ በፕሬዜዳንቱ አቅም ማነስ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ውድቀት መከተሉን እና ሙስና መንሰራፋቱን ይገልፃሉ ፤ በሀገሪቱ ለተፈጠረው የመድሃኒት ፣ የነዳጅ፣ የምግብ እጥረት እና ለድሃው ህዝብ ኑሮ መመሰቃቀልም ፕሬዜዳንቱን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

በሌላ በኩል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን " የሩሲያ ወረራ " ሲሪላንካ ውስጥ ለተፈጠረው ቀውስ አስተዋጽኦ ሳይኖረው አይቀርም ብለዋል። ብሊንከን " የሩሲያ ወረራ ያስከተለው ችግር በየቦታው እየታየ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

መረጃው፦ ከአሶሼትድ ፕሬስ ፣ አርቲ እና ዶቼቨለ የተገኘ ነው።