Get Mystery Box with random crypto!

በፎቶው የምትመለከቱት ቢንያም ኢሳያስ ይባላል። 4 ዓመት ድረስ ፈታኝ ነው የሚባለውን የህክምና ትም | ሰበር ዜና ETHIOPIA

በፎቶው የምትመለከቱት ቢንያም ኢሳያስ ይባላል።
4 ዓመት ድረስ ፈታኝ ነው የሚባለውን የህክምና ትምህርት (ሜዲስን) ከተማረ በኃላ ግን ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በኃላ መማር አትችልም ሲል ገልጾለታል።
ለምን ? ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ ከህፃነቱ ጀምሮ የአካል ጉዳተኛ ነው፤ በዚህም ሳቢያ ነው 5ኛ ዓመት ከደረሰ በኃላ ዩኒቨርሲቲው አካል ጉዳተኛ ስለሆንክ ለዚህ ትምህርት አትመጥንም ብሎ እንዲወጣ የተደረገው።
ይህ ችግር እንዲስተካከል ብዙ ቢለፋም ምንም መፍትሄ አንተገኘም ፤ በዚህ ሁኔታ ትምህርቱን መከታተል የማይችል ከሆነ ለምን በቅድሚያ ትምህርቱን እንዲጀምር ተደረገ ለሚለው ? ዩኒቨርሲቲው መጀመሪያውኑ መመዘን እንደነበረበት ነገር ግን እንዳልመዘነ ገልጿል።
በሌላ በኩል በህክምና ትምህርት ሁለት እጅ የማይጠይቁ ስራዎች ላይ መግባት ችላለሁ ብሎ ተማሪ ቢንያም ቢጠይቅም (ሳይካትሪ፣ ፐብሊክ ሄልዝ ሌሎችም) ዩኒቨርሲቲው ግን ለመቀበል ፍቃደኛ አልሆነም።
ተማሪ ቢንያም ፥ " አጥብቀው ያነሱት ልጅ ማዋለድ፣ ደም የፈሰሰው ሰው ሲመጣ እሱን ማቆም ትችላለህ ? የሚል ጥያቄ ነው የጠየቁኝ፣ ከህፃንነት ጀምሮ አካል ቢጎድለኝም እጄ ይንቀሳቀሳል ይሰራ፣ ቀኝ እጄንም ይደግፈዋል፣ እኔን ለመርዳት ከፈለጋችሁ ስሰራ አይታችሁ እስካሁን ድረስ ትምህርት ስንማር ሁለት እጅ ለሚፈልጉ ስራዎች በራሴ መንገድ መስራት እችላለሁ በህክምና ውስጥ ያሉትንም ጠቅሼላቸዋለሁ ግን ፍቃደኛ አልሆኑም። አትችልም አትችልም ነው አሉኝ። መያዝ ይችላል፣ መደገፍ ይችላል፣ በሁለት እጄ መስራት እችላለሁ፣ እስካሁን ጥሩ ሄጃለሁ በኃላ ያ ሲመጣ በራሴ መንገድ መስራት እችላለሁ ብላቸውም ከእኔ ጋር አብሮ ለመስራት ፍቃደኛ አልሆኑም።
በአጥንት ክፍል evaluate እንድደረግ ላኩኝ ፤ ታህሳስ ውስጥ ነው የጀመረው እስከ ሰኔ ድረስ ቀጥሏል። እስካሁን ቀጥተኝ መልስ ሳይሰጡኝ ነው ያሉት " ሲል ተናግሯል።
አባት አቶ ኢሳያስ ገብረወልድ ልጃቸው በጣም ባለብሩዕ አእምሮ መሆኑን ገልፀው ከታች ጀምሮ በከፍተኛ ውጤት ዩኒቨርሲቲውን እንደተቀላቀለ ገልፀዋል።
አሁን ላይ የተደረገው ድርጊት እጅግ በጣም እንደጎዳቸው አመልክተዋል።
አቶ ኢሳያስ " እንደ አባት ሳይሆን በሙሉ ቤተሰብ ተጎድቷል፣ ከዚህ በፊት ያስተማጉት አስተማሪዎች በጣም ተሰምቷቸዋል፣ ምክንያቱም ይሄ ጉዳይ ያተነሳው ታህሳስ 1 /2014 ነው ቆይቶ ከ2 ወር በኃላ ያለምንም ወረቀት በቃል ነው እንዲወጣ ያሉት " ሲሉ ገልፀዋል።
ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ እንደሚናገረው ዩኒቨርሲቲው አሁን የወሰነው ውሳኔ ሌሎች ትምህርቶች ፋርማሲ፣ ሜዲካል ላብራቶሊ እና ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ እንዲገባ ነው።
ነገር ግን ተማሪ ቢንያም እዛው አሁን ባለበት ቀጥሎ ሁለት እጅ የማይፈልጉ ስፔሻላይዜሽኖች ስላሉ ወደዛ መቀላቀል ነው ፍላጎቱ።
ይሄን ያህል አመት የለፋበትን ከግንዛቤ በማስገባት ወደዛ እንዳያስገቡት ነው የጠየቀው ፤ እነሱ ግን እንደዛ ማድረግ አንልችልም የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።
ተማሪ ቢንያም እና ወልጅ አባቱ ከተፈጠረው ክስተት ጋር በተያያዘ ውሳኔውን ያሳለፉ ዩኒቨርሲቲው አካላት ንቀት በተሞላበት መልኩ እንዳስተናገዱት፣ እንደቀላልም እንዳዩት ቅሬታ አቅርበዋል።

(የቢንያም እና አቶ ኢሳያስ ቃል የተወሰደው ከሸገር ኢንፎ ከተሰኘ የዩትዩብ ቃለምልልስ ነው)