Get Mystery Box with random crypto!

የገሃድ ጾም የገና በዓል ዘንድሮ ዓርብ ይዉላል ዓርብ ይጾማል? ገሃድ ወይም ጋድ በጥምቀትም | Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

የገሃድ ጾም

የገና በዓል ዘንድሮ ዓርብ ይዉላል

ዓርብ ይጾማል?

ገሃድ ወይም ጋድ በጥምቀትም በልደትም አለ አገባቡ ግን ይለያል

ገሃድ ወይም ጋድ ትርጉሙ
መገለጥ፣ መለወጥ፣ ለውጥ፣ምትክ የሚሉ ስያሜዎችን ሲይዝ እንደ አገባቡ ለገናም ለጥምቀትም እንጠቀማለን።

ለገና ሲሆን ገሃድ ምትክ የሚለው ሳይሆን መገለጥ የሚለውን ትርጉም ይይዛል።

ለገና የገና ፆም እስከ በዓሉ ድረስ ስለሚፆም ፆሙ እስከ በዓሉ ዋዜማ ይፆማልና ከዚህ አንፃር በዓሉ በታህሳስ 29 ከሆነ ታህሳስ 28 መጀመሪያውኑ ፆም በመሆኑ ምዕመናን ይፆሙታል

የገና ፆም ምዕመናን ሁሉ ከሰባት ዓመት ጀምሮ እንዲፆሟቸው በአዋጅ ከተደነገጉ ሰባት አፅዋማት አንዱ በመሆኑ ሙሉውን መፆም እንጂ ሲበሉ ቆይተው የመጨረሻዋን ዕለት ገሃድ ናት ማለት ስህተትና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን አለማወቅ ጭምር ነው
ለገና ገሃድ ስንል ምትክ ማለታችን አለመሆኑን መዘንጋት ፈፅሞ የለብንም እና አንዷን ቀን ብቻ መፆም ስርዓተ ቤተክርስቲያን አይደለም።

ለገና ገሃድ ለምን ተባለ ገሃድ መገለጥ፣መታየት ነው ብለናል የክርስቶስ ሰው መሆን መገለጡ፣
አምላክ በድንግል ማህፀን ተወስኖ መገለጡ ወይም መታየቱ ለማብሰር የመጨረሻዋ ቀን ገሃድ ትባላለች
ከላይ እንደ ተመለከትነው መገለጥ፣መታየት የሚለው ትርጉም እዚህ ላይ ግልፅ ይሆናል።

ልክ በአቢይ ፆም ፆመ ህርቃል እንዳለ ፆመ ህማማት እንደሚፆም ሁሉ በገና የጌታችንን ሰው መሆን የጌታን መገለጥ በማሰብ የመጨረሻዋን ቀን ገሃድ እንላታለን

"ልደት ዓርብና ረቡዕ ሲውል ዕለቱ ከጌታ ልደት በላይ ደስታ የለምና፣ከክርስቶስ መወለድ በላይ ሃሴት የለምና አርብ ረቡዕ ፆምነታቸው ይሻራል "

ፍስክ ይሆናል በክርስቶስ መወለድ ያዘነው ሄሮድስ እና ጭፍሮቹ እንጂ ክርስቲያኖች አያዝኑም ፆም ማዘን፣መተከዝ፣መጎሳቆል፣መራብ መጠማት፣መስገድ መድከም ማለት ነውና በጌታ ልደት እነዚህ አይኖሩም

አባቶች እንዲህ ይላሉ
"በጌታ ልደት ማዘን እንደ ሄሮድስና ጭፍሮቹ፣በስቅለቱ መዝፈን እንደ አይሁድ ያስቆጥራል።"

ስለዚህ የገና በዓል ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነውና ዓርብ ረቡዕ ላይ ቢውል ፆምነቱ ተሽሮ ፍስክ ይሆናል

ልደቱን መገለጡን በታላቅ ደስታና ሃሴት እናከብረዋለን።
ቅዳሜና እሁድ ላይ የልደት ዋዜማ ቢውል ከጥሉላት ምግቦች መፆም ግድ ሲሆን ከእህል ውሃ ግን አይጾምም።

በሰላም ያድርሰን፣ አምላካችን ይርዳን

ፍ/ነገሥት አን 15 ቁ 566ና 603