➧....በጣም የሚዋደዱ ባለ ትዳሮች ነበሩ። በፍቅራቸውም ሆነ በታማኝነታቸው ተወዳዳሪ አልነበራቸውም !! በአጋጣሚ ከእለታት አንድ ቀን... #አቶ_ባል ንዴት በተሞላ ቃላት " የኔ እህት " ትሰሚያለሽ ጧት ሲነጋ እዚህ ቤት እንዳላይሽ" የምትፈልጊውንና የምትወጂውን ዕቃ በመያዝ ከቤቴ ውልቅ እንድትይ አሳስብሻለሁ ሁለተኛ አይንሽን ማየት አልፈልግም በማለት ያንባርቅባታል። #ወይዘሮ_ሚስት ➧እንዴት እህት እባላለሁ ሚስትነቱ ቀርቶብኝ " ብላ ኡኡታዋን አቀለጠችው። ሆኖም ግን ወደ ወላጆችዋ ቤት እንድትሄድ የፈቀደላት ንጋት ስለነበረ ምሽቱን ቤቷ በመቀመጥ አሳለፈችው። #አቶ_ባል ➧ ከተኛ የማይነቃ ሰው ነበረና መኝታ ክፍል በመግባት እንቅልፉን ለሽ ብሏል። የሚገርመው ጧት ከእንቅልፉ ሲነቃ እሱነቱን ያገኘው ከሚስቱ ቤተሰቦች ቤት ነበር። እሱም በመደንገጥ ሚስቱን እንዲህ ሲል ጠየቃት " የተኛሁት ከቤቴ ነበር ለመሆኑ እዚህ ማነው ያመጣኝ ?? #ሚስትም እንዲህ አለችው ፦ ሲነጋልሽ የምትወጂውንና የምትፈልጊውን ዕቃ ይዘሽ ውጪ አልከኝ እኔ ደግሞ የምወደውና የምፈልገው አንተ ስለሆንክ እንቅልፍ ከተኛህበት አንስቼ በመሸከም ወደ ቤተሰቦቼ ቤት ይዤህ መጣሁ ስትል መለሰችለት! " ባል በመገረምና በመደሰት የኔ ፍቅር ማታ የተናገርኩት ተናድጄ ነው ይቅርታ አድርጊልኝ ብሎ የኔ ባትሆኚ እንዴት ይቆጨኝ ነበር በማለት ግንባሯን ሳማት። ➧...አዎ! ሴት ልጅ ፍቅርም ይሁን ተንኮል ስትለግስ በእጥፍ ነው ➧ከመጽሐፍ ገፆች @Ethiopian_Top_Inspiration 515 views𝑴𝒓.𝑩𝒆𝒂𝒏, 13:55