2021-10-07 10:16:57
#መውሊድ_ከልካዮች_በብዛት ከሚሰነዝሯቸዉ ማምታቻዎች እና የነርሱ ምላሽ (②)
መውሊድን ከልካዮች እንዲህ ይላሉ፡ ❝መውሊድን ነቢዩ አላከበሩትም ሶሓባዎችም ሆነ ሶሓባዎችን ተክትለው የመጡት “ታቢዒዮችም" አላከበሩትም ስለዚህ ይህ ድርጊት ኸይር/መልካም ቢሆን ኖሮ እነሱ ለዚህ ድርጊት ቃዳሚ በሆኑ ነበር ...❞
=«ምላሽ፦
.
.
.
.
.
.
ለዚህ ንግግራቻው በሸሪዓህ መሰረት ብንፈልግለት አንድም ይህን የሚደግፍ ማስረጃ አናገኝም... ምክኒያቱም በዚህ ንግግራቸው አንድን ነገር ነቢዩ አለማድረጋቸውን ብቻ በማያት ያ ነገር መጥፎ ብሎ መደምደም ነው። ያ ነገር በሸሪዓህ አንፃር ድጋፍ አለው ወይስ የለውም..? በነቢዩ አስተምህሮት መሰረት የተወገዘ ነው ወይስ የሚበረታታ መልካም ተግባር ነው?? የሚለውን በግምት ውስጥ ሳያስገቡትና በሸሪዓህ ሚዛን ሳይለኩት በደፈናው ያንን ነገር እንደጥመት ማሳብና አስከፊ ትችት መለጠፍ ነው። ለዚህ የሙግት መመሪያቸው ማስረጃ ከመኖሩ ይልቅ መመሪያቸውን ውድቅ የሚያደርግ ማስረጃ እንጂ የለም። በዚህ ንግግራቸው በሸሪዓህ እውቀት ምንም ግንዛቤ እንደሌላቸው በጉልህ ያሳያል። ምክኒያቱም #የኡሱል_አልፊቅህ_ዑለማኦች_ቁርኣንና ሐዲስን መሰረት በማድረግ ባውጣጡት መመሪዎች ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነው፦ ”الترك لا يفيد التحريم“ “አንድን ነገር መተው ክልክል መሆኑን አያመላክትም።” ታዲያ በዚህ ምንረዳው ረሱሉ አንድን ነገር አለማድረጋቸው ብቻ ያ ነገር ሐራም መሆንን አያመላክትም። እንደዛውም ስላላደረጉት ብቻ ኸይር ከመሆን አያግደውም።
#በሶሒሕ_አል_ቡኻሪይ_በተዘገበው ሐዲስ እናታችን ዓኢሻህ ረዲየሏሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች፦ « #ነቢዩ_አንዳንድ_ነገራቶችን_በኡመቶቻቸው_ላይ_ግዴታ_እንዳይሆን_በመስጋት_ይተዉት_ነበር_የዱሓን_ሶላት_ነቢዩ_ሲሰግዱ_አላየሁም_እኔ_ግን_እሰግዳለው።»
በዚህ ሐዲስ ደግሞ በውስጡ ብዙ ትምህርት አለበት። ዓኢሻ ረዲየሏሁ ዐንሃ ለሴቶች ባጠቃላይ አዋቂ የነበሩ የሰይዲ አንድን ነገር አለማድራጋቸው ሐራም መሆኑ ቀርቶ መልካም ነገር ከመሆን እንኳን አንደማያግደው በግልፅ ያስረዳል ። ታዲያ ረሱሉ አለማድረጋቸው ራሱ ክልክልነትን የማያመላክት ከሆነ ከዘይኔ በታች ያሉትን መጥቀሱ ለምን አስፈለገ??? አይገርማችሁም በሏህ ይሄ ንቀታቸዉ ህዝቡን ለማደናገርና ሐቅን ላለመቀበል ቢሆን እንጂ..?!
በተጨማሪ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሌላ ሐዲስ እንጥቀስ...
#በዛርና_ሐኪም_በዘገቡት_ሐዲስ ረሱሉሏህ እንዲህ ብለዋል፦ ‹‹አሏህ በመፅሀፉ(በቁርኣኑ) ዉስጥ ሐላል ያለዉ ሁሉ ሐላል፣ሐራም ያለዉ ሁሉ ደግሞ ሐራም ሲሆን፣በዝምታ ያለፈዉ ነገር የተፈቀደ (ዐፍዉ) ነዉ፡፡ ከአሏህ ፈቃዱን ተቀበሉ፡፡ ምክንያቱም ምንንም ነገር አይረሳምና፡፡›› ይህን ካሉ በኋላ ‹‹ጌታህ የሚረሳ አይደለም›› የሚለዉን የቁርአን መልዕክት አነበቡ፡፡››
ሌላ ደግሞ #ዳረል_ቁጥኒይ_በዘገቡት ሐዲስ ረሱሉሏህ እንዲህ ብለዋል፦
‹‹ #አሏህ_ወሰኖችን_አበጅቷልና_አትለፏቸዉ፤ ግዴታ ያደረጋቸዉ ነገሮች አሉና አታጥፏቸዉ (ተግብሯቸዉ) የከለከላቸዉ ነገሮችም አሉና አትዳፈሯቸዉ፤ረስቶ ሳይሆን ለናንተ በማዘን በዝምታ ያለፋቸዉ ነገሮችም አሉና ስለነርሱ አትፈላፈሉ፡፡››
በዚህ ሐዲስ ምንረዳው ረሱሉ ሳይተገብሯቸውና ሳይጠቅሷቸው ያለፏቸው ነገሮች ሆነው የተፈቀዱ እንደሆኑ ነግረዉናል።
በመጨረሻም ለመውሊድ ከልካዮች ማምታቻ አጥጋቢ ምላሽ የሚሆን እንጥቀስ ። እሱም ሰይዱና ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንህ) ወደ ሰይዲ አቡበክር አሲዲቅ(ረዲያሏሁ ዐንህ) መጥተው ቁርኣንን በአንድ ላይ የመሰብሰብ ጉዳይ ላይ ሲያማክሯቸው ፤ ያኔ ሰይዲ አቡበክር አሲዲቅ መጀመሪያ ላይ፡ “ #እንዴት_ነቢዩ_ያላደረጉትን_አደርጋለው?”ብለው ነበር ከዛም ዐመር አሏቸው፡ (ልብ በሉ እዚህ ጋር) “ይህ እኮ ኸይር/መልካም ስራ ነው።” ከዚያ በኋላ ሰይዲ አቡበክር ይህንን ሀሳብ ተቀብለው ቁርኣንን ለመጀመሪያ ግዜ የሰበሰቡ ሆነዋል።
ተመልከቱ እዚህ ጋር ሰይዲ ዑመር "ይህ እኮ ኸይር/መልካም ስራ ነው።" ሲሉ.. ቁርኣንን መሰብሰብ ነቢዩ ባያደርጉትም ኸይር እንደሆነ ነው። ሰይዲ አቡበክርም ይህንን ሀሳብ ተቀብለው ቁርኣንን መሰብሰባቸው ነቢዪ አንድን ነገር አለ ማድረጋቸው መጥፎ እንዳልሆነ ከታላላቅ ኹለፋኡ-ራሺዲኖች ምስክር ነው።
በተጨማሪም በዚህ ክስተት የምንቀስመው ነገር ... ሰይዱና ዑመር ይህንን ንግግር ሲሏቸው ሰይዲ አቡበክር كل بدعة ضلالة በማለት አልተከራከሩም! ወይ ደግሞ ዲናችን ሙሉእ ነው ምንም ጭማሪ አይፈልግም ብለውም አልተከራከሩም ወይም ነቢዩ ያላደረጉት ስለሆነ ይህ ነገር ጥመት ነው አይቻልም ብለውም አልተሟገቱም!።
#ታዲያ_እነሆ_መውሊድን_የሚትከለክሉ ፡ “ቁርኣንን በአንድ ላይ ነቢዩ ሰብስበዋል?....... ወይ ደግሞ አዘዉታል?!!. ታዲያ አቡበክር ከነቢዩ ተሽለው ነው?....ወይስ አቡበክር ያደረጉት ነገር መጥፎ ሆኖ ነው ነቢዩ ያላደረጉት?!..”
ትክክለኛና ሚዛናዊ አካሄድ አንድ ድርጊት ጥሩነቱና መጥፎነቱ ሚመዘነው ለቁርኣን እና ለሐዲስ ተስማሚ መሆኑን አለመሆኑን በማየት ነው። ሰይዲ አቡበክርም ረዲየሏሁ ዐንሁ ይህንን ድርጊት ያፀደቁት የሚከተለውን ሐዲስ መሰረት በማድረግ ነው፦ ረሱሉሏህ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ «በእስልምና ውስጥ ‹ለመልካም ግኝት› ፈር ቀዳጅ የሆነ ሰው የበጎ ስራውን ምንዳ ያገኛል ፤ እንዲሁም ከሱ በኋላ እሱን ተከትለው (ይህንን መልካም ስራ) የሰሩ ሰዎች የሚያገኙትንም አጅር መሳይ ከአጅራቸው ምንም ሳይቀነስ ያገኛል። በእስልምና ውስጥ ለመጥፎ (መጥፎ ግኝት) ፈር ቀዳጅ ለሆነ ሰው በመጥፎ ስራው ኃጢያት ይኖርበታል ፤ እንዲሁም ከሱ በኋላ እሱን ተከትለው (ይህንን መጥፎ ስራ) ለሰሩ ሰዎች የሚኖርባቸውን ኃጢያት መሳይ ከኃጢያታቸው ምንም ሳይቀንስ በሱ ላይ ይኖርበታል»። ከጀሪር ኢብን ዐብዲላህ ሙስሊም ሶሒሓቸው ውስጥ ዘግበውታል።
« #መልካም_ቢሆን_ኖሮ_እንዴት_ነቢዩ_አላወቁትም?" የሚሏትን መሰረት የለሽ ጥያቄ ይህ ሐዲስ እና ከላይ የጠቀስናቸው ማስረጃዎች ውድቅ ያደርገዋል። እንደዛውም ማኛውም ኸይር ነገር ነቢዩ ባይሰረቱም ሸሪዓን ከተስማማ መልካም እንደሆነ ያስረዳናል።
ሲቀጥል ደግሞ፡ አንድን ነገር ክልክል ነው ለማለት ግዴታ ለክልክልነቱ የቁርአን እና የሐዲስ ማስረጃን ይጠይቃል። ይህ ድርጊት ከቁርኣን እና ከሐዲስ ጋር የሚገጥም ከሆነ የሚበቃ ይሆናል ቢድዐአቱል ሐሰናህ ሲባልም ይህ ማለት ነው።
═════━
ለሌሎች በማስተላለፍ ተደራሽነቱን እናስፋ
Share Share Share Share
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች
┏━ ━━━━ ━┓
በቴሌግራም አድራሻችን
https://telegram.me/nisaulmesharie
On YouTube
Facebook
https://www.facebook.com/nusaulmesharie* /
┗━ ━━━━ ━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
133 views07:16