Get Mystery Box with random crypto!

እስከመቼ ግን በኢትዮጲያ ቡና ዙሪያ ሀሳብ የምንሰጥው ግለሰብ ጠልተን አልያም የማንወደው ሰው | ቡናችን👆

እስከመቼ ግን

በኢትዮጲያ ቡና ዙሪያ ሀሳብ የምንሰጥው ግለሰብ ጠልተን አልያም የማንወደው ሰው በክለቡ ዙሪያ ስላለ አልያም የሆነ ቡድን ለማጠልሸት ወይም ስራ ለማጥላላት ወይም ስለኢትዮጲያ ቡና  ከኛ በላይ የሚያስብ ሰው የለም እያልን  አይደለም::

ስለኢትዮጲያ ቡና እድሜ ልካቸውን የሰሩለትን እና የደከሙለትን ሰዎች ክብርንም ለመንካት ወይም ስራቸውንም ለማቃለል አይደለም:: ግን ኢትዮጲያ ቡና የብዙ ሚሊዮን ደጋፊዎችን ልብ ቤተሰብ የሚነካ ብዙ ደጋፊዎች የአካልም የህይወትም መስእዋትነት የከፈሉለት ህዝባዊ ክለብ ነው ::

አሁንም በርካቶች የግልም ሆነ የቤተሰብ ህይወታቸውን ጭምር ጥለው ለቡድኑ መስውአትነት እየከፈሉ ነው ያለው !

.....ሆኖም ግን ከተመሰረተ 47 አመት የሞላው የንጋት ኮከብ  ክለባችን ትላንት ከተመሰረቱት ክለቦች እንኳን መወዳደር አቅቶት እንደዚህ ወርዶ ሲንኮታኮት ማየት በእጅጉ ያማል !!!

...የሚመለከተን አካላቶች በሙሉ በቡድን እርስ በርስ ከመበሻሸቅ ወጥተን በተከባበረ እና በሚያግባቡን ቋንቋዎች እንነጋገር ከእልህ ወጥተን ክለባችንን በሚያድን መድሀኒት እንረባርብ አለም የደረሰበትን የእግር ኳስ ሳይንስ የሚከተል ዘመናዊ እና ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ቡድን የሚከተለውን መዋቅር እንትከል እንዲሁም እንከተል!!

ኢትዮጵያ ቡና እንደዚህ ሆኖ ማየት ስለሚያመን ሁሌም እንናገራለን !!

  እትዮጲቡና መዋቅራዊ ለውጥ ያስፈልገዋል እባካችሁን እባካችሁን ራሳችሁን ፈትሹ!

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc