Get Mystery Box with random crypto!

የፖለቲካ እና ጦር ተሿሚዎች ‘አጋፋሪ፡ አጋፋሪ ከዘበኞች ጋር በመሆን በጌታው ላይ ማንም እንዳይነ | ጦብያን በታሪክ

የፖለቲካ እና ጦር ተሿሚዎች

‘አጋፋሪ፡ አጋፋሪ ከዘበኞች ጋር በመሆን በጌታው ላይ ማንም እንዳይነሳ፣ ከእልፍኝ አስከልካይ ጋር በመሆን ደግሞ የጌታውን እና ቤተሰቡን ደኅንነት ይጠብቃል። ዋና ሥራው እስረኞችን መጠበቅ፣ አዳራሽ ውስጥ ነገሮችን መከታተል እና ቤት ውስጥ ያለውን ሕግ እና ደምብ ማስጠበቅ ነበር። የቤት ውስጥ ባሪያዎች እና ሰራተኛውች ከውጭ ጋር የሚያደርጉትንም ግንኙነት ይከታተላል።

ጌታው ከቦታ ወደ ቦታ እየሄደ ከሆነ እና ችሎት የሚቆም ከሆነ አጋፋሪው በጌታው ፈንታ ሰላምታ ይሰጣል፣ ለተሰበሰበውም ስለ ጌታው ቸርነት፣ ፈሪሃ እግዜር እና ፍትሕ አዋቂነት ገለጻ ይሰጣል። አጋፋሪው የጌታውን ልብስ፣ ነጋሪቶች እና ሌሎች ሹማምንትንም ሁኔታ ይከታተላል። በጉዞ ላይ የድንኳን አተካከልንም እሱ ይቆጣጠራል። ደስታ የሚባለው እና የንጉሠነገሥቱ የሆነው ቀይ ድንኳን ሲተከል በዘመቻ ጉዞ ላይ ያለው ጦር መቆም እንዳለበት ምልክት ስለሆነ ወዲያውኑ ነጫጭ እና ጥቋቁር ድንኳኖች ይተከላሉ። እያንዳንዳቸው የሹማምንትን ሥልጣን እና ኃይል ያሳያሉ። ነጭ ድንኳኖች የአጋፋሪ፣ የብላቴን ጌታ እና የጥቃቅን ብላቴን ጌታዎች ናቸው። የውስጥ አሽከር አለቃ እና ረዳቱ አዛዥ ጥቋቁር ድንኳኖችን ይተክላሉ።

የአጋፋሪው ሌላ ዋና ሥራ ከብላቴን ጌታው እና ከጥቃቅን ብላቴን ጌታው ጋር በመሆን አዳዲስ ጨዋ ወታደሮችን እድገት እና ሥልጠና መከታተል ነበር። ብላቴን ጌታ የሚባል ሹመት የተሰጠው ሰው ዲፕሎማሲያዊ ብቃት ያለው፣ መካከለኛ እድሜ ላይ ያለ፣ ብዙ መሬት የተሰጠው እና የሐር ልብስ የሚለብስ በየስብሰባዎች የሚገኝ ሲሆን የጌታውን ወጣት ጦረኞች እንክብካቤ ይቆጣጠራል። ረዳቱ እኚህን ጨዋዎች የቤተመንግሥት ጸባይ ያስተምራቸዋል።’

ፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት
ገጽ 177—78