Get Mystery Box with random crypto!

‘ሕፃናት አደን የሚለማመዱት በወንጭፍ እና በጦር ሲሆን ከአስር ዓመት ጀምሮ ያሉት ደግሞ መሣሪያ እ | ጦብያን በታሪክ

‘ሕፃናት አደን የሚለማመዱት በወንጭፍ እና በጦር ሲሆን ከአስር ዓመት ጀምሮ ያሉት ደግሞ መሣሪያ እየተሰጣቸው የሚበሉ እንስሳትን — ማለትም እነቆቅ፣ ጅግራን፣ ሶረኒን ማደን ይለማመዳሉ። ድፋርሳ፣ ድክድክ፣ አጋዘን፣ ቀጭኔ፣ ድኩላዎችንም እያደኑ ይመገባሉ። ረሃብ እና ድርቅ በሚመጡበት ጊዜ እነዚህን እንስሳት እያደኑ መመገብ የተለመደ ነበር።

በአደን ላይ ያሉ ጦረኞች ደክዬ እና ሰጎኖች የጦር ውርወራ መለማመጃዎቻቸው ነበሩ። የሰጎን እንቁላሎች የአብያተ ክርስቲያንን እና ቤቶችን ጣሪያዎች ያስጌጣሉ፤ ጦረኞች እና አዳኞች ደግሞ
የሰገንን ላባ ወይንም ሶራን ይጌጡበታል።

በቆላማ አካባቢ አደን ማደን በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ ዱር በሚባሉ ሥፍራዎች እየሄዱ ማደን የድፍረት መለማመጃዎች ነበር። ለዚህም ነው እንዲህ ተብሎ የሚገጠመው፡

«ዱብ ዱብ ይላል እንደበረዶ
በልጅነቱ በረሃ ለምዶ»

እጅግ አስቸጋሪ ክልሎች እየገቡ ማደን ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ፈይዳው ትልቅ ነበር።

«ቢገድልም ገደለ ባይገድልም ገደለ
እበረሃ ወርዶ ጦም ውሎ ካደረ»፣

«መናኝና አዳኝ አብረው ገሰገሱ
አዳኝም ለግዳይ መናኝም ለነፍሱ»።’

ፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት
ገጽ 159—160