Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ጀርመኑ ጂአይዜድ ስምምነት ተፈራሙ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴ | Ethiopia buna sport clubʳ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ጀርመኑ ጂአይዜድ ስምምነት ተፈራሙ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጀርመኑ የልማት ተቋም ጂአይዜድ (GIZ) ጋር በፌዴሬሽናችን ሥር የሚገኘው የካፍ የልህቀት ማዕከል የመጫወቻ እና ልምምድ ሜዳን ደረጃ ለማሻሻል እንዲሁም አዲስ ተጨማሪ ሜዳ ለመሥራት የሚያስችል የ10 ሚልየን ብር ስምምነት በትናንትናው ዕለት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሠረት ጂአይዜድ በካፍ የልህቀት ማዕከል የሚገኘውን የመጫወቻ ሜዳ ደረጃውን የጠበቀ መልኩ የመልሶ ግንባታ ሥራ የሚያከናውን ሲሆን አንድ ተጨማሪ አዲስ ሜዳ ደግሞ የሚገነባ ይሆናል። ከመልሶ እና አዲስ ግንባታው በተጨማሪ ለጥገና እና እንክብካቤ ሠራተኞች የሚሰጠው ስልጠናም የስምምነቱ አካል ነው።

@ethiopiabuna12t
@ethiopiabunasportteam